ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሐኪም ቤት ገባ-ቤተሰቦቹ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2009ማስታወቂያ
በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ዝዋይ ባቱ ሐኪም ቤት እንደገባ ተሰምቷል። የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለዶይቸ ቬለ ዛሬ እንደገለፀዉ ጋዜጠኛ ተመስገን በምን ኹኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ ወደ ሐኪም ቤቱ ሄደው ቢጠይቁም መግባት እንደተከለከሉ ገልጧል።
ታሪኩ ጋዜጠኛ ተመስገንን ካለፉት ዐሥር ቀናት አንስቶ ማየት እንዳልቻሉ፥ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝም እንደማያውቁ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይገኝበታል የተባለው የባቱ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኑራ ነገዎ «እንደዛ የሚባል ሰው እኛ ጋ አልገባም» ሲሉ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ