1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት እና የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ መልዕክቶችዋ

ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2018

በጋዜጠኝት ሞያ ፋና ብሮድካስቲንግ ወደ ስምንት ዓመት ገደማ አገልግላለች። በቅርቡ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይ በህብረተሰብ ዘንድ የሚሰሙ እንከኖችን ማለትም ህፀጽፆችን ነቅሳ አዉጥታ በምትለቃቸዉ ትምህርት አዘል፤ ቪዲዮዎችዋ ታዋቂነትን እያተረፈች ነዉ። ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር።

https://p.dw.com/p/5E8vS
ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር
ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር ምስል፦ Privat

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር እና የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መልዕክቶችዋ

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዋ ታዋቂዋ ጋዜጠኛ        

«እኔ እንግዲህ የመንግሥት ሚዲያዉስ ሆኜ ስንነካቸዉ የሚቆረቁራቸዉ፤ ለአንድ ሃገር ለአንድ ሚዲያ እየሰራን እራሱ የሚጎረብጣቸዉ፤ ኢትዮጵያስትይ የሚያንዘረዝራቸዉ፤ አንድነትዋ ስትይ የሚከፋቸዉ ሰዎች አሉ።»

በጋዜጠኝት ሞያ ፋና ብሮድካስቲንግ ወደ ስምንት ዓመት ገደማ  አገልግላለች። በቅርቡ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይ በህብረተሰብ ዘንድ የሚሰሙ እንከኖችን ማለትም ህፀጽፆችን ነቅሳ አዉጥታ በምትለቃቸዉ ትምህርት አዘል፤ ቪዲዮዎችዋ ታዋቂነትን እያተረፈች ነዉ። ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር። ሣልሳዊት በቪዲዮ የምታሰራጫቸዉ መልዕክቶች አንድነትን፤ ሰላምን፣ መደጋገፍን ኢትዮጵያዊነትን ብሎም የኢትዮጵያ ታሪክን የያዙ ናቸዉ። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ዝግጅቶቿን የሚከታተሉ፤ “ሣልሳዊት ምርር ያለ የሀገር ፈቅር ከእውቀት ጋር ያቀናጃት፤ ለጥራዝ ነጠቆች ቅስም መስበሪያ ለእውነተኛ ዜጎች ደግሞ አንጀት የሚያርስ ኩራት የምትሰጥ፤ እባክሽ ሣልሳዊት አትጥፊብን።” ሲሉ አስተያየት ይጽፉላታል። ይህንኑ የተሰጧትን አስተያየቶች ሳታይ የቀረች አይመስልም፤ በቅርቡ በሰፊዉ በሁሉም አይነት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዝግጅቶችዋን ለማሰራጨት ዝግጅቷን እያጠናቀቀች መሆኑን ተናግራለች።

ይህንኑ ይዘን ጋዜጠኛ ሣልሳዊትን፤ በዶቼ ቬለ በእንግድነት ለማቅረብ ፈልገን ጥያቄ ስናቀርብላት አላንገራገረችም። በደስታ ብላ ቀጠሮ ሰጥታ በቀጠሮዋ ተገኘች።  እንዴት ይህን ታሪክ አዘል ዝግቶች፤ የምታያቸዉን ግድፈቶች የምታርምበት ዝግጅት ለማሰራጨት ወሰነች፤ ይሆን?

ኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝዋ

«በመጀመርያ ደረጃ ምንድን ነዉ የሚለዉን ነገር፤ ሰዎች ምን እየሰሩ ነዉ የሚለዉን ነገር እመለከታለሁ። ምክንያቱም፤ የማነሳቸዉ ርዕሶች በጣም ከባድ ጉዳዮች ናቸዉ። ምንም ወዳጅ የሚፈራበት ርዕስ አይደለም። ሁሉም ሰዉ እንድታስደስችዉ፤ እሱን የሚፈልገዉን ነገር እንድትናገሪለት ይፈልጋል። ትንሽ ከባድ ነዉ፤ ግን እንደ ጋዜጠኝነቴ በመንግስት ሚዲያ ዉስጥ ሆኜ ስንነካቸዉ የሚቆረቁራቸዉ፤ ለአንድ ሃገር ለአንድ ሚዲያ እየሰራን እራሱ የሚጎረብጣቸዉ፤ ኢትዮጵያ ስትይ የሚያንዘረዝራቸዉ፤ አንድነትዋ ስትይ የሚከፋቸዉ ሰዎች አሉ። እና እነዚህን በነበረኝ የስምንት ዓመት የጋዜጠኝነት ቆይታ፤ እየመዘገብኩ እይዛቸዉ ነበር።

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር
ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር ምስል፦ Privat

የትኞቹ ነገሮች እንደማይደፈሩ ለምን እንደዛ እንደሆነ፤ በዚህ ላይ ታሪክን የማወቅ ፍላጎቴ እየጨመረ መጣ። የኔ ሞያ ጋዜጠኝነት ነዉ። አገር ወዳድ የምላቸዉ፤ በአገር አንድነት የሚያምኑ፤ በምንም በማንም እጃቸዉ ያልተጠመዘዘ፤ምሁራኖችን አነጋግራለሁ።»  

ዶቼ ቬለ ከጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር ጋር ረዘም ያለ ቆይታ አድርጓል፤ ሙሉዉን ቃለ ምልልስ የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ