1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዜጠኛ ሙህየዲን አብዱላሂ በዋስ ተለቀቀ

ሐሙስ፣ ግንቦት 11 2014

ትናንት ከእስር በዋስ ከተፈታ በኃላ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ አስተያየት የሰጠው ጋዜጠኛ ሙህየዲን ለእስር ስላዳረገው ነገር የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እና ከታሰረ በኃላ" መንግስት ላይ ህዝብን አነሳስተሀል" የሚል ክስ እንደቀረበበት ገልጧል።

https://p.dw.com/p/4BYPB
Äthiopien |Journalist Muhaddin Abdulahi
ምስል Privat

ጋዜጠኛ ሙህየዲን አብዱላሂ በዋስ ተለቀቀ

 ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በእስር ላይ የቆየው ጋዜጠኛ ሙህየዲን አብዱላሂ ትናንት በዋስ ከእስር መለቀቁ ተሰምቷል። ጋዜጠኛው ከሚሰራበት የሀረሪ ክልል ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ የተወሰደው።  ለእስር የሚያበቃ ምንም ድርጊት አለማከናወኑን ለዶይቼ ቬሌ የገለፀው ሙህየዲን ከታሰረ በኃላ "መንግስት ላይ ህዝብን አነሳስተሀል" የሚል ክስ እንደቀረበበት ጠቅሷል። ትናንት በዋስትና ከእስር ቢፈታም " አሁንም ፍርሀቶች አሉብኝ" ሲል ተናግሯል።  ጋዜጠኛ ሙህየዲን የድሬደዋው ወኪላችን መሳይ ተክሉ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ትናንት ከእስር በዋስ ከተፈታ በኃላ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ አስተያየት የሰጠው ጋዜጠኛ ሙህየዲን ለእስር ስላዳረገው ነገር የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እና ከታሰረ በኃላ" መንግስት ላይ ህዝብን አነሳስተሀል" የሚል ክስ እንደቀረበበት ገልጧል። ከሚሰራበት መሥሪያ ቤት በፀጥታ ኃይል የተያዘው ጋዜጠኛ ሙህየዲን ከአያያዝ ጀምሮ የነበረው ሂደት ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሶ በኃላም ዋስትና ስለተፈቀደበት ሁኔታ አስረድቷል። በፍርድ ቤት የአስራ አራት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበት ከእስር በዋስ የወጣው ጋዜጠኛ ሙህየዲን ማስፈራሪያዎች እንዳሉበት በመጥቀስ በቀጣይም ፍርሀት እንዳለበት ለዶይቼ ቬሌ ተናግሯል።  

መሳይ ተክሉ 

ልደት አበበ
ኂሩት መለሠ