1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ቢያንስ 30 ሰዎች ተገድለዋል

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 26 2013

በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ፤ ቀጮ ክራክር እና ጋሌ ቀበሌ ማንነት ላይ ባነጣጠረ የታጣቂዎች የግፍ ጭፍጨፋ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። አረመኔያዊው የጅምላ ግድያ የተፈጸመው በጥይት እና በሳንጃ መሆኑንም ነዋሪዎች ገልጠዋል።

https://p.dw.com/p/3sxSV
Karte Sodo Ethiopia ENG

አረመኔያዊው ግድያ የተፈጸመው በጥይትና በሳንጃ ነው

በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ፤ ቀጮ ክራክር እና ጋሌ ቀበሌ ማንነት ላይ ባነጣጠረ የታጣቂዎች የግፍ ጭፍጨፋ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። አረመኔያዊው የጅምላ ግድያ የተፈጸመው በጥይት እና በሳንጃ መሆኑንም ነዋሪዎች ገልጠዋል። ከአካባቢው ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሕይወታቸውን ለማትረፍ የተሰደዱ ነዋሪዎች አሁንም ድረስ ስጋቱ ማንዣበቡን ይናገራሉ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ሥዩም ጌቱ ነዋሪዎቹን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

ዓርብ ሚያዚያ 15 ቀን፣ 2013 በደረሰው ጥቃት ሲቪል ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ያረጋገጡት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጣሂር ኢብራሂም እስከ ሚቀጥለው ሳምንት ከአከባቢው የሸሹትን ማኅበረሰብ ወደየቀዬያቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ከአከባቢው ተፈናቅለው በተለያዩ ከተሞች ላይ የተጠለሉት ተጎጂዎች ግን አሁንም አከባቢው ከስጋት አለመጽዳቱን በመግለጽ፤ ጥለውት የወጡ ንብረቶቻቸው በሙሉ መዘረፉንም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከጥቃቱ በኋላ በስፍራው የደረሱት የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ሊደርስ የነበረውን ተጨማሪ ጉዳት መቀነሳቸውን መረዳቱንና በአከባቢው ላይ ግን ሰራተኞቹን ለመላክ አለመቻሉን መግለጹ ይታወሳል።

ሥዩም ጌቱ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ