1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችና መዋዕለ ሕጻናትን መከፈት ጀመረች

ሰኞ፣ የካቲት 15 2013

ላለፉት ሁለት ወራት ተዘግተው የከረሙት የጀርመን የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችና መዋዕለ ሕጻናት ዛሬ መከፈት ጀመሩ። ዛሬ በከፊል ትምህርት ቤቶች የተከፈቱት ከሁለት ሳምንታት በፊት መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የየፌደራል ግዛቱ አስተዳዳሪዎች የኮሮና ቀውስን የተመለከተ ስብሰባ አካሂደው በተስማሙት መሠረት ነው።

https://p.dw.com/p/3pinm
Deutschland Berlin | Coronavirus | Schüler, Rückkehr Präsenzunterricht
ምስል Abdulhamid Hosbas/Anadolu Agency/picture alliance

ላለፉት ሁለት ወራት ተዘግተው የከረሙት የጀርመን የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችና መዋዕለ ሕጻናት ዛሬ መከፈት ጀመሩ። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከጀርመን 16 ፌደራል ግዛቶች ከግማሽ በላይ በሚሆኑት ግዛቶች ትምህርት ቤቶች ዳግም በራቸውን ለተማሪዎች መክፈታቸው ሥራቸውን ከቤት ለመሥራት ለተገደዱ ወላጆች መጠነኛ እፎይታ ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል። በደቡብ ምዕራብ ጀርመን ፍራንከንታል ከተማ የሚኖሩት የአንደኛ ደረጃ መምህርት አንያ ኔስሊንግ ይህንኑ ነው የገለፁት፤
«ልጆች ወደትምህርት ቤት ሲመለሱ በማየቴ ደስ ብሎኛል። ልጆቹ በጣም ለረዥም ጊዜያት በቤታቸው ነበሩ እናም ለወላጆቻቸው በጣም ከባድ ፈተና ነበር። በመጨረሻም ዛሬን በመጀመሩ በእርጥም ደስተኞች ነን።»
ዛሬ በከፊል ትምህርት ቤቶች የተከፈቱት ከሁለት ሳምንታት በፊት መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የየፌደራል ግዛቱ አስተዳዳሪዎች የኮሮና ቀውስን የተመለከተ ስብሰባ አካሂደው በተስማሙት መሠረት ነው። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት አሁንም በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንዳንድ አካባቢዎች ቀንሶ ቢታይም የተበራከተባቸውም አሉ። የጀርመን የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ተቋም ባለፉት 24 ሰዓታት 4,369 አዲስ በተሐዋሲው የተያዙ ሰዎች ሲገኙ፤ 62 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ማለፉን አመልክቷል። 

ሸዋዬ ለገሰ

አዜብ ታደሰ