1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን በኮሮና ምክንያት የጀመረችዉን የድንበር ቁጥጥር አበቃች

ሰኞ፣ ሰኔ 8 2012

ጀርመን የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ስታደርግ የነበረዉን የድንበርዋ ቁጥጥር  ከትናንት እሁድ ለሊት ለሰኞ አጥብያ እኩለ ለሊት ጀምሮ የድንበር ቁጥጥሩን ሙሉ በሙሉ መነሳትዋን አስታወቀች። የተለያዩ አዉሮጳ ሃገራትም ድንበሮቻቸዉን እየከፈቱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3doXi
Coronavirus Ende der Kontrollen an der Grenze zwischen Straßburg und Kehl
ምስል DW/B. Riegert

 

 

ጀርመን የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ስታደርግ የነበረዉን የድንበርዋ ቁጥጥር  ከትናንት እሁድ ለሊት ለሰኞ አጥብያ እኩለ ለሊት ጀምሮ የድንበር ቁጥጥሩን ሙሉ በሙሉ መነሳትዋን አስታወቀች። የተለያዩ አዉሮጳ ሃገራትም ድንበሮቻቸዉን እየከፈቱ ነዉ። የጀርመኑ የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴር ዜ ሆፈር  እንደተናገሩት  ከሦስት   ወራት በፊት ጀምሮ በጀርመን ድንበሮች የነበረዉ ቁጥጥር ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተነስቶአል። ጀርመን ከስምንት የአዉሮጳ ሃገራት ጋር  ድንበር እንደምትጋራ ይታወቃል። በሌላ በኩል የኮሮና ተኅዋሲን ስጋት በተመለከተ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት ጉዞ ማስጠንቀቅያ በሚል ከሦስት ወራት ጀምሮ አዉጦት የነበረዉን ማስጠንቀቅያም አንስቶአል። በበጋ ወራት እረፍታቸዉን ኦስትርያ፤ ኢጣሊያ፤ ክሮየሽያ፤ ግሪክ እንና ፈረንሳይ የሚያሳልፉት አብዛኛ  ጀርመናዉያን ዜናዉ እፎይታን ፈጥሮላቸዋል ተብሎአል። ከአንድና ከሁለት ሳምንት ጀምሮ  ለበጋ ወራት የእረፍት ጊዜ በጀርመን የተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሮቻቸዉ  ስለሚዘጉ ዜናዉ ወላጆች ልጆቻቸዉን ወደ እረፍት ቦታ ለመዉሰድ ጥሩ ዜና ሳይሆን እንዳልቀረም  ተመልክቶአል።  

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ