ጀርመን ለኢትዮጵያ 352 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠች
ሰኞ፣ ኅዳር 22 2012ማስታወቂያ
ጀርመን የኢትዮጵያን የምጣኔ-ሐብት ማሻሻያዎች ለመደገፍ 352.5 ሚሊዮን ዩሮ ($388 ሚሊዮን) የገንዘብ ድጋፍ ሰጠች። የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር የኢትዮጵያ የፋይናንስ ምኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የጀርመን የኤኮኖሚ ትብብር እና ልማት ምኒስትር ጌርድ ሙለር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ስምምነት ተፈራርመዋል። በፊርማው ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተገኝተዋል።
ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ «ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግብርናን ዘዴ ለማሻሻል ይረዳ ዘንድ ድጋፍ እንዲደረግ በጠየቁት መሠረት የጀርመን መንግሥት የለገሳቸው መለዋወጫ የተሟላላቸው የ144 የግብርና መሣሪያዎችን ቁልፎች የርክክብ ሂደት በሚመለከታቸው አካላት መካከል» መፈጸሙን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
ኂሩት መለሰ