1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን 1,500 ተጨማሪ ስደተኞች ልትቀበል ነው

ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2013

ጀርመን በግርክ ደሴቶች ተጠልለው ከሚገኙ ስደተኞች ውስጥ ተጨማሪ 1500 ያህሉን የመቀበል ዕቅድ እንዳላት አስታወቀች። ጀርመን ተጨማሪ ስደተኞችን ለመቀበል ከውሳኔ የደረሰችው ግርክ የሚገኘው ሞርያ የስደተኞች መጠለያ ጣብያ በእሳት ከጋየ እና በርካታ ስደተኞች ያለመጠለያ መቅረታቸውን ተከትሎ ነው።

https://p.dw.com/p/3iVix
Griechenland | Nach Brand in Flüchtlingslager Moria auf Lesbos
ምስል picture-alliance/dpa/S. Baltagiannis

ጀርመን በግርክ ደሴቶች ተጠልለው ከሚገኙ ስደተኞች ውስጥ ተጨማሪ 1500 ያህሉን የመቀበል ዕቅድ እንዳላት አስታወቀች። ጀርመን ተጨማሪ ስደተኞችን ለመቀበል ከውሳኔ የደረሰችው ግርክ የሚገኘው ሞርያ የስደተኞች መጠለያ ጣብያ በእሳት ከጋየ እና በርካታ ስደተኞች ያለመጠለያ መቅረታቸውን ተከትሎ ነው። በዚህም ልጆች ያላቸው ቤተሰቦች እና በግሪክ የስደተኞች አስተዳደር መስፈርቱን አሟልተው የተገኙትን ለመቀበል የተዘጋጀውን ዕቅድ መራሔተ መንግስት አንጌላ ሜርክል እና የሀገር ውስጥ ሚንስትሩ ሆርስት ዚሆፈር ተቀብለውታል። ስደተኞቹን ለመቀበል ጀርመን በያዘችው ዕቅድ ላይ ቀደም ሲል ከግሪክ ጋር ተመክሮ ከስምምነት መደረሱን የጀርመን ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። ወደ 12,000 የሚጠጉ ስደተኞችን አስጠልሎ በነበረው የግሪኩ የሞርያ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ሆን ብሎ በእሳት እንዲቃጠል መደረጉ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ለመቀበል ኃላፊነቱን አንወስድም በሚል በህብረቱ አባል ሀገሮች ዘንድ አዲስ ክርክር አስነስቷል። ይህ በእንዲህ እያለ የሞርያ መጠለያ ጣብያን በእሳት አቃጥለዋል ተብለው የተጠረጠሩ አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የግሪክ ፖሊስ አስታውቋል። በአደጋው እጁ ሳይኖርበት አይቀርም የተባለ ሌላ አንድ ግለሰብንም በማፈላለግ ላይ መሆናቸውን ባለስልጣናቱ መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ