1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀማሪ ኩባንያዎችን ከባለወረቶች ለማገናኘት የወጠነው የጋራ ፖርታል

ዓርብ፣ ግንቦት 12 2014

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ያዘጋጀው የጋራ ፖርታል "ሥራ ፈጣሪዎችን ለመርዳት ሁሉንም የሥራ ሥነ-ምህዳራዊ ባለድርሻዎች የሚያገናኝና የኢንቨስትመንት ልምድን ለማሳደግ መሠረት የሚጥል ነው።" በማስተርካርድ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ በተደረገለት ፕሮጀክት ከ340 በላይ ጀማሪ ኩባንያዎች እና ወደ 62 ኢንቨስተሮች እንደሚገኙ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4Bdv3
Äthiopien | Diskussion über politische und ethnische Konflikte - Ministerin Muferiat Kamil
ምስል Yohannes G. Egziabher/DW

ጀማሪ ኩባንያዎችን ከባለወረቶች ለማገናኘት የወጠነው የጋራ ፖርታል

በኢትዮጵያ በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከተመድ ፓርታል ፕሮጀክት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በመሆኑ የስራ እድል ፈጣሪዎችን ከኢንቨስተሮች ጋር ለማገናኘት የመሰረተው የጋራ ፖርታል የተሰኘው ፕሮጀክት ውጤት እያመጣ ነው ተባለ፡፡

ሚኒስቴሩ የፕሮጀክቱን የአንድ ኣመት አፈጻጸምን ትናንት በገመገመበት ወቅት እንዳለው ፕሮጄክቱ ባለሃብቶችን ከስራ እድል ፈጠራ ሀሳብ አምንጪዎች ጋር ከማገናኘትም ባሻገር የገንዘብ ማስገኛ ምንጭ በመሆኑ ለስራ እድል ፈጠራ ተስፋ ሰጪ ፍሬ አምትቷል ነው ያለው፡፡

ወጣት ሮዛ ካሳ ይህን በመላው አገሪቱ ለቱሪስቶች እና ለማንኛውም እንግዳ የጉዞ ሁኔታን ቀለል የሚያደርገው ለራሳቸው ደግሞ የስራ እድል ፈጠራ የሆነላቸውን መተግበሪያ ፈጥረው፤ የንግድ ሀሳቡንም ይዘው፤ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከተመድ የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር ባዘጋጀው የስራ ፈጠራ ሀሳቦች እና መዋዕለ ንዋዩን የያዙትን ኢንቨስተሮች ለማገናኘት ባዘጋጀው መድረክ አግኝቼ ሳነጋግራት ያጋራችኝ አስተያየት ነው፡፡ የጋራ ፖርታል የተሰኘው ኢንቨስተሮችን ከስራ እድል ፈጠራ ባለሙያዎች ጋር የሚያገናኘውን ለመቀላቀል ያበቃትንም ምክኒያት እንዲህ ታስረዳለች፡፡ 
በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ በወርቅ ማሽነሪ ማምረት እና ማዕድን ፍለጋ ላይ የተሰማራውና የጋራ ፖርታልን ከአንድ ዓመት በፊት የተቀላቀለው ዮብሳን አረጋም ስለ የጋራ ፖርታል ጠቀሜታው እንዲህ አስተያየቱን አጋራን፡፡ 

አማኑኤል ለማ የጋራ ዶት ኦርግ ፕሮጀክት ቴክኒካል አማካሪ ነው፡፡ ስለ የጋራ ፕሮጀክት ፋይዳ እና ዓላማም ጠይቀናቸው ነበር፡፡ እንደ ባለሙያው ገለጻ ፕሮጀክቱ የቢዝነስ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች ገንዘብ ከያዙት ጋር በማስተሳሰር ሁሉንም ተጠቃሚ በማድረግ ሰፊ የስራ እድል ፈጠራን ያስፋፋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከተመሰረተ ከአንድ ኣመት በኋላ ስላመጣው ውጤት እና ክፍተቶቹን ለመገምገም የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴት ትናንት በአዲስ አበባ ባዘጋጀው መድረክ ላይ የስራ ፈጠራ ባለሙያዎች እና ኢንቨስተሮች ተገናኝተውበታል፡፡ 

መድረኩ የስራ እድል ፈጣሪዎችን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ አይነተኛ ሚና እንዳለው የሚገልጹት የስራ እና ክልሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ፕሮጀክቱ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ኣመት ተስፋ ሰጪ እምርታ ማሳየቱን አመልክተዋል፡፡ 

ስዩም ጌቱ 
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ