ድሬዳዋ፣ የምርጫ ዝግጅት
ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013ማስታወቂያ
በመጪው ሰኔ ድሬደዋ ዉስጥ ሊደረግ በታቀደዉ ምርጫ እንደሚወዳደሩ የኢትዮጵጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቁ።ባለፈዉ ሳምንት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ በድሬዳዋዉ ምርጫ ለመወዳደር ዕጩ ያስመዘገበ ተቃዋሚ ፓርቲ እንደሌለ አስታዉቀዉ ነበር።የኢዜማና የአብን ባለስልጣናት ዛሬ በየፊናቸዉ እንዳሉት ግን በምርጫዉ የሚወዳደሩ ዕጩዎቻቸዉን አስመዝግበዋል፤ ለማስመዝገብ እየተዘጋጁም ነዉ።
መሳይ ተክሉ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ