1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድሬዳዋ ዛሬ ተረጋግታለች 

ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 2010

የድሬዳዋው ነዋሪ፣ መሬታችን ተወሰደብን በሚል የተቀሰቀሰው የዚህ ግጭት መሠረታዊ መነሻ የሁለቱ ክልሎች ወሰን በትክክል ተለይቶ አለመታወቁ ነው ይላል።የድሬዳዋ አስተዳደር የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በየነ ግን ከዚህ ቀደም የሁለቱ ክልሎች ባለሥልጣናት በተገኙበት ወሰን የማካለሉ ሥራ እንደሚከናወን ተገልጿ እንደነበር ያስታውሳሉ።

https://p.dw.com/p/32TIr
Stadt Dire Dawa in Äthiopien
ምስል Hailegzi Mehari

ድሬዳዋ ዛሬ ተረጋግታለች 

በድሪዳዋ ከተማ በተለይም ገንደ ተስፋ በተባለው አካባቢ ከትናንት በስተያ ተቀስቅሶ ትናንት በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎችም የንብረት ውድመት ያስከተለው ግጭት መብረዱን ነዋሪዎች እና የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ «በተሳሳተ መረጃ ተነሳ» ባሉት ግጭት ንብረት ከመውደሙ ውጭ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ግን የለም። 
ሐምሌ 23፣ 2010 ዓም ነበር ከሶማሌ ክልል በሚዋሰነው የድሬዳዋው አስተዳደር «ገንደ ተስፋ» ግጭት የተቀሰቀሰው። የተጋጩትም መሬታችን አለአግባብ ተወስዷል የሚሉ የገንደ ተስፋ ወጣቶች እና ከወሰኑ ወዲያ ያሉ የሶማሌ ክልል ወጣቶች ናቸው። በሁለቱ ወገኖች መካከል የተካሄደው ይኽው ግጭት እስከ ትናንት ማምሻ ድረስ ነበር የዘለቀው። አንድ የከተማዋ ነዋሪ ግጭቱ ምን ይመስል እንደነበረ ለዶቼቬለ አስረድቷል። የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ በፍቃዱ በየነ የከተማዋ ነዋሪ ያለውን አረጋግጠው ግጭቱ ሊቀሰቀስ የቻለው ግን ለኅብረተሰቡ ደረሰ ባሉት የተሳሳተ መረጃ ሰበብ መሆኑን ተናግረዋል። «የገንደ ተስፋው»ግጭት ትናንት የፀጥታ ኃይላት እና የሀገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ከገቡ በኋላ ቢረጋጋም ከአጎራባች ክልል መጥተዋል የተባሉ ወጣቶች በመኪና በድሬዳዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የድሬዳዋው ነዋሪ ለዶቼቬለ ገልጿል። ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንድ የቀድሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ባለሥልጣን ቤት ይገኝበታል። የድሬዳዋው ነዋሪ፣ መሬታችን ተወሰደብን በሚል የተቀሰቀሰው የዚህ ግጭት መሠረታዊ መነሻ የሁለቱ ክልሎች ወሰን በትክክል ተለይቶ አለመታወቁ ነው ይላል።የድሬዳዋ አስተዳደር የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በየነ ግን ከዚህ ቀደም የሁለቱ ክልሎች ባለሥልጣናት በተገኙበት ወሰን የማካለሉ ሥራ እንደሚከናወን ተገልጿ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ መረጃ ለኅብረተሰቡ እንዲደርስ አለመደረጉ ግን ለትናንትና ወዲያ ለትናንቱ ግጭት መንስኤ ሆኗል። አቶ ፈቃዱ እንዳሉት በግጭቱ ንብረት ከመጎዳቱ በስተቀር የሰው ሕይወት አልጠፋም። እንደ አቶ ፈቃዱም ሆነ እንደ ከተማዋ ነዋሪዎች ድሬዳዋ  ዛሬ ተረጋግታለች። ለወደፊቱም መሰል ግጭቶች እንዳይነሱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ሥራ እያከናወኑ ነው ብለዋል አቶ ፈቃዱ።

Äthiopien Alte Eisenbahnverbindung
ምስል DW/Y. Gebreegziabher
Äthiopien Stadt Dire Dawa
ምስል DW/T. Waldyes

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ