1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዳግም ጦርነት የመቀስቀስ ሥጋት

ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2014

«ፃነትና እኩልነት ፓርቲ ለዳግም ጦርነት መነሳሳት በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ብሏል። ችግሩ በሰላም እንዲፈታ መንግሥት የድርድር ፍኖተ ካርታ እንዲያዘጋጅና ወደ ተግባር እንዲገባም ጠይቋል ።

https://p.dw.com/p/4BTfy
Karte Sodo Ethiopia ENG

ዳግም እንዳይነሳ የተሰጋው ጦርነት በኢትዮጵያ

በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል ዳግም ጦርነት የመቀስቀስ ሥጋት ተፈጥሯል። ኢትዮጵያን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ያስገባትና ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ዘልቆ ለወራት ጋብ ያለው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሥጋት ዳግም ማንዣበቡ እንዳሳሰባቸው ክገለፁ አካላት መካከል አንዱ «ፃነትና እኩልነት ፓርቲ»ው።

ፓርቲው ለዳግም ጦርነት መነሳሳት በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ብሏል። ችግሩ በሰላም እንዲፈታ መንግሥት የድርድር ፍኖተ ካርታ እንዲያዘጋጅና ወደ ተግባር እንዲገባም  ጠይቋል ።

በሁለቱ ወገኖች መካከል ጦርነት ተመልሶ የማገርሸቱ እውነት አይቀሬ ይመስላል ያሉ አንድ የፖለቲካ እና የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ተንታኝ ጦርነቱ ከተከሰተ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን አጠናክሮ ችግሩ በዘላቂነት የሚፈታበት ወይም አሸናፊው ሳይታወቅ የውጭ ኃይሎች ጭምር ተዋናይ የሚሆኑበት አውድ ይፈጠራል አልያም ሀገሪቱ ለተራዘመ ቀውስ የምትዳረግበት እውነት ሊከሰት እንደሚችል ተናግረዋል። 

ሰሎሞን መጬ 
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር 
ኂሩት መለሰ