ዲሽታ-ጊና፤ የታሪኩ ጋንኪስ የእንዋደድ ዜማ
እሑድ፣ ሚያዝያ 10 2013ድምፃዊ ታሪኩ ጋንኪሳ በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ 16 ብሄረሰቦች መካከል አንዱ በሆነው በአሪ ብሄረሰብ ቋንቋ «ዲሽታ ጊና» በሚል በቅርቡ አዲስ ተወዳጅ ዜማ ለአድማጭ ጀሮ አድርሷል ። «ዲሽታ ጊና» በአሪ ብሄረሰብ ዘንድ በጥር ወር የሚከበር የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን፤ በዓሉ የመረዳዳት፣ የአንድነትና የዕርቅ በዓልም ጭምር ነው።ድምፃዊው ይህንን በዓል በተመለከተ ሙዚቃ መስራት የፈለገውም አንድም የብሄረሰቡን ባህል ለማስተዋወቅ በሌላ በኩል ደግሞ ፍቅር፣ ሰላምና መተሳሰብ በኢትዮትዮጵያውያን መካከል እንዲሰፍን ካለው ምኞት መሆኑን ይገልጻል።
ድምፃዊ ታሪኩ ጋንኪሳ ተወልዶ ባደገባት ጅንካ፤ በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኦሞ የባህል ቡድን ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቡድኑ ውስጥ የተለያዩ ባህላዊ ዜማዎችን በመጫወት ላይ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደምምም «ውቧ ጅንካ» የሚል ነጠላ ዜማ ለአድማጭ ጀሮ አብቅቷል።
በሙዚቃው ከአድማጩ ያገኘው ምላሽ «ህዝቡ ምን ያህል ፍቅርና ሰላም እንደናፈቀው።» የሚያሳይ ነው የሚለው ታሪኩ፤ በሀገሪቱ ዕርቅ፣ፍቅር፣ አንድነትና ሰላም እንዲሰፍን የሚያደርጉ ሙዚቃዎችና ሌሎች የኪነ-ጥበብ ሥራዎች እንዲሰሩ በማገዝ መንግስት የበኩሉን ቢወጣ መልካም መሆኑን ገልጿል።
ሙሉ ዝገጀቱን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ፀሀይ ጫኔ
ማነተጋፍቶት ስለሺ