1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ይመሰረታል የተባለዉ አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድን 

ረቡዕ፣ ግንቦት 11 2013

በሀገሪቱ የነበረው የፀጥታ አወቃቀር “ግራ የተጋባ፣ ስርዓቱ የተዛባና አስተሳሰቡ ልክ ያልሆነ ስለነበር ህዝቡ በእጅጉ ሰላም ርቆት ቆይቷል ” ሲል የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፣ አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድንና የህብረተሰብ ደህንነት ቅኝት በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚቋቋምም ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

https://p.dw.com/p/3tczR
Äthiopien | Logo  Ministry of Peace
ምስል DW/G. Tedla

“ግራ የተጋባ፣ ስርዓቱ የተዛባና አስተሳሰቡ ልክ ያልሆነ ስለነበር ህዝቡ በእጅጉ ሰላም ርቆት ቆይቷል ”

ይመሰረታል የተባለዉ አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድን 

የነበረው የፀጥታ አወቃቀር “ግራ የተጋባ፣ ስርዓቱ የተዛባና አስተሳሰቡ ልክ ያልሆነ ስለነበር ህዝቡ በእጅጉ ሰላም ርቆት ቆይቷል ” ሲል የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፣ አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድንና የህብረተሰብ ደህንነት ቅኝት በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚቋቋምም ሚኒስቴሩ አመልክቷል፣ አደረጃጀቱ ቅርበትን ሰለሚፈጥር ውጤታማ እንደሚሆን አንድ የግጭት መከላከልና አፈታት ባለሙያ ተናግረዋል፡፡አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድንና የህብረተሰብ ደህንነት ቅኝት ለመመስረት በሰላም ሚኒስቴርና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ባሕር ዳር ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው እንዳሉት ከዚህ በፊት የነበሩት የፀጥታ ተቋማት አደረጃጀታቸው ግራ የተገባና የተዛባ ነበር፡፡