1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያልታወጀዉ አዋጅ

ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2012

የተሰራጨዉ መግለጫ የሚንስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ከመግለፁ በስተቀር የተደነገበትን ዕለት፣ ዝርዝር አፈፃፀሙንም ሆነ የሚፀናበትን ጊዜ አልጠቀሰም።የተድበሰበሰዉ መግለጫ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።

https://p.dw.com/p/3aelM
Äthiopien Unterzeichnung eWTP Hub
ምስል DW/Y. Gebrezihaber

የያልታወጀዉ አዋጅና የባለሙያዎች አስተያየት

የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት የኮሮና ተሕዋሲ ሥርጭትን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን የጠቅላይ ሚንስትሩ ፅሕፈት ቤት ዛሬ አስታዉቋል።በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ስም በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ የተሰራጨዉ መግለጫ የሚንስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ከመግለፁ በስተቀር የተደነገበትን ዕለት፣ ዝርዝር አፈፃፀሙንም ሆነ የሚፀናበትን ጊዜ አልጠቀሰም።የተድበሰበሰዉ መግለጫ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።ስለጉዳዩ በጠቅላይ ሚንስትሩ ፅሕፈት ቤት የቃል አቀባይ ቢሮ (ፕሬስ ሴክሪታሪያት ነዉ-የሚሉት እነሱ) ባለስልጣናት ማብራሪያ እንዲሰጡን ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ስልክ ብንደዉልም ልናገኛቸዉ አልቻንም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ የሕግ ባለሙያዎች ሥላልታወጀዉ አዋጅ የሰጡትን አስተያየትን አጠናቅሯል።የጠቅላይ ሚንስትር ፅሕፈት ቤት ዛሬ ከቀትር በኋላ ያሰራጨዉ መግለጫም ግራ የሚያጋባ ነዉ።መጋቢት 30 2012 (ዛሬ ማለት ነዉ) የሚንስትሮች ምክር ቤት 8ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉን መግለጫዉ ያወሳና፣ ስለ አስቸኳይ አዋጁ አስፈላጊነት በሰፊዉ ካተተ በኋላ የሚከተለዉን ሐረግ ያክላል።
«የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል። ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ጥቂት ማስተካከያዎችን በማከል ከዛሬ 29/07/2012 ዓም ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡» ይላል። መጋቢት ሰላሳ ተሰበሰበ የተባለዉ የሚንስትሮች ምክር ቤት «ዛሬ» የሚለዉ መጋቢት 29ኝ ነዉ።ትናንትን።

ዮሐንስ ገብረእግዛኢአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ