1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያልተለወጠው የፖለቲካ ባህል በኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ጥቅምት 10 2012

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ በትኩረት ከሚከታተሉ አንዳንዶች የመክበብ ፖለቲካ ሲሉት፣ አንዳንዶች ሕዝቡ ለውጥ ብሎ የመጣውን ሁሉ እያመነ በተስፋ የሚመለከት፣ መንግሥት ሥልጣን ላይ ትኩረት አድርጎ የሕዝብን አደራ ችላ የሚልበት አካሄድ እንዳለው ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3RXhi
Karte Äthiopien Ethnien EN

ያልተለጠው የፖለቲካ ባህል በኢትዮጵያ

ለአንዳንዶች ደግሞ ትግሉ በማን እና በማን መካከል ነው የሚለውን ለመግለፅ የማይቻል ውል አልባ ነው። ሁሉንም የሚያስማማው ግን አሁንም የሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ባለበት የሚረግጥ፤ ጫፍ እና ጫፍ ተቆሞ መጓተት፤ መቧደን የበዛበት አይነት መሆኑ ነው። ከ50 ዓመታት በላይ ለተጨቆነው ሕዝብ ለውጥ ለማምጣት የተደረጉ ትግሎች ምንም አላስገኙም ማለት አይቻልም። ሆኖም ግን መሠረታዊው እና ሁሉም የሚመኙት፤ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት አስተዳደር የመመሥረቱ ነገር ግን አሁንም ከፍላጎት አልፎ እውን የመሆኑ ጉዳይ ረዥም መጓዝን እንደሚጠይቅ እየታየ ነው። የሃሳብ ልዩነት ዛሬም እንደ1960 እና 70ዎቹ ያፋጥጣጥ፣ ያፈራርጃል። ውሎ አድሮ ሊመጣ የሚችለውን በመስጋት አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል የመለኮት ኃይልን ጣልቃ ገብነት የሚመኝበት እውነት በገሀድ ይታያል። በዚህ መሃል ኅብረተሰቡ ለውጥ የተሻለ ነገር ለማየት ይመኛል። ያልተለወጠው የፖለቲካ ባህል በኢትዮጵያ  የዚህ ሳምንት የእንወያይ ርዕሰ ጉዳይ ነው።

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ