1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የፖምፒዮ ንግግር

ረቡዕ፣ የካቲት 11 2012

ፖምፒዮ  አዲስ አበባ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪቃ  የምጣኔ ሐብት ኮሚሽን አዳራሽ ለተሰበሰቡ የአፍሪቃ ባለሐብቶችና ነጋዴዎች እንደነገሩት ለአፍሪቃ የሚሰሩ ትላልቅ የመሰረተ ልማት አዉታሮች ሐገራትን ዕዳ ዉስጥ እየዘፈቁ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3Y0aZ
Kolumbien Anti-Terror-Konferenz in Bogota | Mike Pompeo
ምስል AP

የፖምፒዮ ንግግር ለአፍሪቃ ባለሐብቶች

የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ የአፍሪቃ ሐገራት ከአምባገነኖች አገዛዝና «ባዶ» ካሉት የምጣኔ ሐብት ዕድገት ተስፋቸዉ አንዲጠነቀቁ መከሩ።ፖምፒዮ  አዲስ አበባ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪቃ  የምጣኔ ሐብት ኮሚሽን አዳራሽ ለተሰበሰቡ የአፍሪቃ ባለሐብቶችና ነጋዴዎች እንደነገሩት ለአፍሪቃ የሚሰሩ ትላልቅ የመሰረተ ልማት አዉታሮች ሐገራትን ዕዳ ዉስጥ እየዘፈቁ ነዉ።የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የአፍሪቃን ገበያ በተቆጣጠረችዉ በቻይና ላይ ባነጣጠረ  ንግግራቸዉ አምባገነን ገዢዎች ብልፅግናን፣ ሉዓላዊነትና ዕድገትን ሳይሆን ሙስናን፣ጥገኝነትንና አለመረጋጋትን ያሰፍናሉ።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ