የፖላንድ ዜጎች በብሪታንያ የገጠማቸው ችግር
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 1 2008ማስታወቂያ
በብሪታንያ የሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ካለፈው ሰኔ ወር በኋላ 16 ጊዜ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈፅመዋል። የፖላንድ እና የብሪታንያ ባለስልጣናት አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው ስለዚሁ ጉዳይ በተደጋጋሚ ተወያይተዋል። አንድ የፖላንድ የልዑካን ቡድን አሁንም ለንደን፣ ብሪታንያ ይገኛል። የልዑካን ቡድን በብሪታንያ ያሉትን ዜጎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚቻልበትን መፍትሔ የማፈላለግ ዓላማ ይዞ ነው ወደ ለንደን የተጓዘው።
ስለሺ ይልማ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ