1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በድሬደዋ 

ማክሰኞ፣ ግንቦት 3 2013

በመጪው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬደዋ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መስርተዋል። በስምምነቱ ላይ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢዘገይም የጋራ ምክር ቤቱ መመስረት እና ሰነዱ መፈረሙ በከተማዋ የሚካሄደው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል  ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3tG3A
Äthiopien Neun Parteien etablieren gemeinsamen Rat
ምስል Messay Teklu/DW

«ሰነዱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል»

በመጪው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬደዋ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መስርተዋል። በስምምነቱ ላይ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢዘገይም የጋራ ምክር ቤቱ መመስረት እና ሰነዱ መፈረሙ በከተማዋ የሚካሄደው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል  ብለዋል።

ገዢው ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ በመጪው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬደዋ አስታዳደር ከሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘጠኙ ተገኝተው በመሰረቱት የጋራ ምክር ቤት ምስረታ መድረክ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን ፖለቲካ ፓርቲዎች ለመደማመጥ እና ለመከባበር ትኩረት መስጠት እናዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች እስከታችኛው አደረጃጀታቸው አውርደው ለተግባራዊነቱ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክልል ምክር ቤት እጩ የሆኑት አቶ ዮናስ በትሩ ቢዘገይም ስምምነቱ መፈረሙ ጠቃሚ እና በከተማዋ የሚካሄደው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል፡፡

የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ተወካይ አቶ ጀማል ዑመር በበኩላቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የበለጠ ተቻችለን ከመተነኳኮል እና ከመወቃቀስ ይልቅ ያሉትን ችግሮች እየፈታን እንድንሄድ ያግዛል የሚል አስተያየት ሰተዋል፡፡

በድሬደዋ ለፌደራልና እና ለከተማዋ ምክር ቤት ህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በምርጫው ይሳተፋሉ፡፡

መሳይ ተክሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ