1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክት ምዝገባ

ዓርብ፣ ጥር 14 2013

ለምርጫ 2013 ዓ.ም. የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታቸውን መምረጥ ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሔረዊ ምርጫ ቦርድፓርቲዎች ለምርጫው የሚወከሉበት ምልክት ላይ ቅሬታ ካላቸው እስከ ጥር 24 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. ድረስ እልባት እንደሚያገኝ ዛሬ ለብዙኃን መገናኛ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3oJ17
Logo | National Election Board of Ethiopia
ምስል National Election Board of Ethiopia

የምርጫ ምልክት መረጣ እስከ ጥር 18 ቀን፣ ብቻ ይቆያል

ለምርጫ 2013 ዓ.ም. የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታቸውን መምረጥ ጀምረዋል። ትናንት ጥር 13 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. በተጀመረው የምርጫ ምልክት መረጣ እስከ ጥር 18 ቀን፣ ብቻ ይቆያል ያለው የኢትዮጵያ ብሔረዊ ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲዎች ለምርጫው የሚወከሉበት ምልክት ላይ ቅሬታ ካላቸው እስከ ጥር 24 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. ድረስ እልባት እንደሚያገኝ ዛሬ ለብዙኃን መገናኛ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን ቦርዱ ካዘጋጀው አልበም ውስጥ ሳይመርጡ ቀርተው በግላቸው ይወክለኛል ያሉትን ምልክት ማቅረብ ካሻቸውም ከተቀመጠው የሕግ ማዕቀፍ ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን ይኖርበታል ተብሏል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሥዩም ጌቱ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ሥዩም ጌቱ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ