1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ተጠባቂው ውጤት

ዓርብ፣ ጥቅምት 6 2013

በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባትን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ፍኖተ ካርታ ይፈጥራል ተብሎ እየተካሄደ ያለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ እስካሁን የሚጠበቅበትን ፍሬ አለማምጣቱን ፖለቲከኞች ገለጹ፡፡

https://p.dw.com/p/3k1dc
20.06.2013 DW Online Karten Basis Aethiopien spanisch

በዉይይቱ ሊደረስባቸው የማይችሉ የማይመስሉ ነጥቦችም ጭምር ተነስተዋል

በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባትን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ፍኖተ ካርታ ይፈጥራል ተብሎ እየተካሄደ ያለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ እስካሁን የሚጠበቅበትን ፍሬ አለማምጣቱን ፖለቲከኞች ገለጹ፡፡ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦ.ፌ.ኮ.) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንደሚሉት በሃገሪቱ ተቋማት የሚመሩት በገዢው ፓርቲ ፍኖተ ካርታ ይሁኝታ በመሆኑ መሰል ውይይቶች የተቀናቃኞችም ምልከታን ለማካተት የሚያስችሉ መሆን ይገባዋል ነው የሚሉት፡፡

ቀጣዩን ብሔራዊ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ በማድረግ ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን መሆን መሰረት የምጥል ነው የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ አሁን በሃገሪቱ እየተከናወኑ ያሉት የፖለቲካ ምህዳርን የማስፋት ጥረት ሙሉ  ተስፋ እንዳልሰጣቸውም ይገልጻሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በመድረኩ ከስምምነት ሊደረስባቸው የማይመስሉ ነጥቦችም ጭምር ተነስተው እየተመከረባቸው ነው ሲሉ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህባራዊ ፍትህ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ በመድረኩ ተስፋ ሰጪ ውይይቶች እየተደረጉ ቢሆንም እስካሁንም የተቀመጠ የመፍትሄ ሃሳብ አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

ስዩም ጌቱ 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ