1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ አራማጆች ውይይት ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 8 2012

የተለያዩ የፖለቲካ አራማጆች (አክቲቪስቶች) የተሳተፉበት ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሄደ። የ“ሃሳብ ማዕድ” በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ በተደረገው በዚህ ውይይት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተዋል።  

https://p.dw.com/p/3RZlp
Äthiopien Addis Abeba | Diskussion zu politischen Aktivisten
ምስል DW/Y. Gegziabher

የፖለቲካ አራማጆች ውይይት ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ

ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ የፖለቲካ አራማጆች (አክቲቪስቶች) “ማዳመጥ፤ መረዳት፤ መናገር፤ መግባባት” የሚሉ እሳቤዎችን በመንተራስ የ“ሃሳብ ማዕድ” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ውይይት አደረጉ። የፖለቲካ አራማጆቹ “ጽንፈኝነት ሀገር የሚበታተን ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። 

በውይይቱ ላይ 12 የፖለቲካ አራማጆች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አተያዮች እንደ መነሻ ሀሳብ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በዛሬው ውይይት ጎልቶ ከተነገረው ውስጥ “የፖለቲካ አራማጅነትን እና ጋዜጠኝነትን አደባልቆ መሄድ ተገቢነት የለውም” የሚለው አንዱ ነው። በአንጻሩ “ስርዓቱ ሳይሻሻል እንዲህ አይነት አስተያየት መስጠት ተገቢነት የለውም” የሚሉም ነበሩ።   

የውይይት ሀሳቡ አመንጪ እና የመድረኩ አደራጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት “ዋና አላማው በማህበራዊ እና በመደበኛ መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚጽፉ፤ የሚታወቁ፣ ብዙ ተከታታይ ያላቸው ሰዎች ተቀራርበው፣ አንድ ላይ ቁጭ ብለው እንዲያወሩ ማድረግ ነው” ሲል ለዶይቼ ቬለ (DW) ተናግሯል። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር

ተስፋለም ወልደየስ