የፖለቲከኞች ጦር ግንባር የመዝመት ውሳኔ
ረቡዕ፣ ኅዳር 15 2014ማስታወቂያ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር መሄድ የኢትዮጵያን ድል ያፋጥናል ብሎ እንደሚያምን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ ( ኢዜማ ) ተናገረ። ከፍተኛ አመራሮቹን ጨምሮ አባላትና ደጋፊዎቹ ወደ ጦር ግንባር እንዲዘምቱ ትናንት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የወሰነው ኢዜማ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው እንዲህ ባለው ጊዜ ለሀገር ህልውና በጋራ መቆም ምርጫ የሌለው ግዴታ ነው ብሏል።አንድ የፖለቲካ ሳይንስ አዋቂ በበኩላቸው የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በጦርነት ለመጨረስ ያስገደደው ያቀረበው የሰላም አማራጭ ተቀባይነት አለማግኘቱና የተወሰኑ ምዕራባውያን ሃገራት ጦርነቱን ቀጣናዊ ለማድረግ ጣልቃ መግባታቸው ነው ብለዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ