1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲከኞቹ ከእስር መለቀቅና ለሃገሪቱ ፖለቲካ ያለዉ ተስፋ

ማክሰኞ፣ ጥር 3 2014

ፖለቲከኞች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መለቀቃቸዉ ኢትዮጵያ ወደ ብሔራዊ ውይይት ለማምራት ኃይል ሊሆናት እንደሚችል ተገለጸ። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኞ እንደሚሉት መሰል ውሳኔዎች ኢትዮጵያ አሁንም ለምትጋፈጠው ግጭት እልባት ሊያመጣ ይችላል፡፡

https://p.dw.com/p/45O71
Äthiopien Oromo Federalist Congress
ምስል Seyoum Getu/DW

የፖለቲከኞቹ መፈታት ለሰላምና አንድነት መልካም ጅማሮ ነዉ


ከ 18 ወራት በላይ የታሰሩ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በክስ ሂድት ላይ የነበሩ ፖለቲከኞች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መለቀቃቸዉ ኢትዮጵያ ወደ ብሔራዊ ውይይት ለማምራት ኃይል ሊሆናት እንደሚችል ተገለጸ። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኞ እንደሚሉት መሰል ውሳኔዎች ኢትዮጵያ አሁንም ለምትጋፈጠው ግጭት እልባት ሊያመጣ ይችላል፡፡  ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኞ እንደሚሉት መሰል ውሳኔዎች ኢትዮጵያ አሁንም ለምትጋፈጠው ግጭት እልባት ሊያመጣ ይችላል፡፡
ባለፈው ዓርብ ምሽት በሶስት የተለያዩ የክስ መዝገቦች ተከፍቶባቸው የነበሩት ፖለቲከኞች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መለቀቃቸውን ተከትሎ ሙገሳም ነቀፌታም እየተሰማ ነው፡፡ ሰሞኑን አቋማቸውን በመግለጫም ያረጋገጡት ኢዜማ፣ አብን እና እናት ፓርቲን የመሳሰሉ የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይም አሁንም ድረስ መንግስትን የሚዋጋው የህወኃት አመራር የነበሩ ፖለቲከኞች መለቀቃቸውን አጣጥለው መንቀፋቸው ይታወሳል፡፡ በአቶ ጃዋር መሃመድ መዝገብ ስር ሲከሰሱ የነበሩ ፖለቲከኞቹ የተለቀቁለት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ግን አሁናዊውን የመንግስት እርምጃ አበጀ ብሎታል፡፡ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት የፖለቲከኞቹ መፈታት ለሰላምና አንድነት መልካም ጅማሮ ሲሉ ገልጸውታል፡፡ 
አቶ ሙላቱ በተመሳሳይ ሁኔታ በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ በአገሪቱ የፖለቲካ እስር ላይ የሚገኙ ያሏቸው ተፈተው የአገሪቱ ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈታም ጠይቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅጣጫዋን ይቀይር ይሆናል በሚል የታመነበት የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ሂደት ላይ ባለችበት ባሁን ወቅት ፖለቲከኞቹን መፍታቷ በጎ እርምጃ ነው የሚሉት የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር አቶ ሰለሞን ተፈራ በበኩላቸው፤ ሂደቱ እርቅ ወደ ሚያመጣው የብሔራዊ መግባባት የሚወስድ ሊሆን እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ዶቼ ቬለ ከእስር የተለቀቁ የተለያዩ ፖለቲከኞችን ለማነጋገር ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው በቀጥታ ለማነጋገር አልተቻለም፡፡ ዛሬ በኦፌኮ ኦፊሲያላዊ ገጽ የተሳሳተ እስር ላይ ከነበሩ የፖለቲካ አመራሮች በሚል በተሰጠው የጽሁፍ መግለጫ፤ በኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ የሚሳተፉ ተፋላሚ ኃይላት የሰላም አማራጭ እንዲፈልጉ ይጠይቃል፡፡ መግለጫው ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ከጦርነት ይልቅ ሰላም የሚመጣበትን መንገድ እንዲደግፉም ጠይቋል፡፡ አክሎም የፖለቲካ እስረኞች ያሏቸው ሁሉ እንዲፈቱ እና ለሰላማዊ ትግል ሰፊ ስፍራ እንዲሰጥም አትቷል ባለ ሶስት ገጽ መግለጫው፡፡  

Äthiopien I Jawar Mohammed
ምስል Mulugeta Ayene/AP Photo/picture alliance


ስዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ