1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፓዌ አካባቢ አርሶአደሮች ቅሬታ

ዓርብ፣ መስከረም 16 2012

በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ተብለው ከስድስት ዓመት በፊት መሬታቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ተመጣጣኝ ካሳ እንዳተሰጣቸው ገለጹ፡፡ አንድ አንዶች ደግሞ ምትክ መሬት አልተሰጠንም ብለዋል፡፡ በፓዌ ወረዳ ይገነባል የተባለው የስኳር ፋብሪካም ሥራ አለመጀመሩን ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3QMKT
Äthiopien - Weltrekord im Bäume pflanzen -Symbolbild
ምስል picture-alliance/G. Fischer

የፓዌ አካባቢ አርሶአደሮች ቅሬታ

በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ተብለው ከስድስት ዓመት በፊት መሬታቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ተመጣጣኝ ካሳ እንዳተሰጣቸው ገለጹ፡፡ አንድ አንዶች ደግሞ ምትክ መሬት አልተሰጠንም ብለዋል፡፡ በፓዌ ወረዳ ይገነባል የተባለው የስኳር ፋብሪካም ሥራ አለመጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል አዊ ዞንና በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ፓዌ ወረዳ የሚገነባው የጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ሥራ ሲጀምር ከ 1300 በላይ አርሶ አደሮች ከማሳቸው መነሳታቸውን ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የኢትዩጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን አካል የሆነው የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ75ሺ ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሥራ ሲጀምር ወደ ሌላ አካባቢ የተዛወሩት በፓዌ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች   ተገቢውን ምትክ መሬት ወይም ካሳ አልተሰጠንም ብለዋል፡፡ ለስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ግንባታ ተብለው ከመኖሪያ ይዞታቸው  ወደ ልላ ቦታ ሲዛወሩ ከተቋሙም ተመጣጣኝ የካሳ ክፍያ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ምክንያት ከፓዌ መንደር 7 ተነስተው ህዳሴ ሰፈር በተባለ ቦታ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የሰፈሩበት አከባበቢ ለኑሮና ለእርሻ የማይመች ነው ይላሉ፡፡ ወደ አካባቢው ከመዛወራቸው በፊት የነበራቸው መሬት እስከ አምስት ሄክታር የሚደርስ መሆኑን የተናገሩት የልማት ተነሺዎቹ አሁን የተሰጣቸው መሬት ደግሞ ሁለት ሄክታር ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቅሬታቸውን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውን ነው የገለጹት፡፡

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖረሽን መረጃ ለማግኘት በስልክ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን ኮርፕሬሽኑ ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ለፕሮጀክቱ ግንባታ ተብሎ ከመኖሪያቸው ለተነትሱ ካሳ  ይገባቸዋል ለተባሉት  አርሶ አደሮች በሙሉ፤ ተገቢውን ካሳ መክፈሉን ገልጾ ነበር፡፡ የአርሶ አደሮቹን ቅሬታ በተመለከተ ያነጋገረኳቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አዲጎ አምሳያ በበኩላቸው አርሶ አደሮቹ መሬትን አስመልከቶ የሚቀርቡ ቅሬታዎች መኖራቸውን አስታውቀዋአል፡፡  ነገር የልማት ተነሺዎቹ የሚያቀርቡት የካሳ ጥያቄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ክልሉ አርሶ አደሮቹ በጠየቁት መሰረት ምለሽ መሰጡትን ገልጸዋል፡፡

 

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ