የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ታገደ
ዓርብ፣ ነሐሴ 22 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ የወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች እንዳይለቀቁ አቃቤ ሕግ በመቃወሙ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ገቢር ሳይሆን ቀረ።ባለፈዉ ሰኔ በተቀሰቀሰዉ ሁከትና ግጭት ተጠርጥረዉ የታሰሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ደጀኔ ጣፋ እና 3 የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ጋዜጠኞች እያንዳዳቸዉ በ10 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ባለፈዉ ሰኞ ወስኖ ነበር።ይሁንና አቃቤ ሕግ ይግባኝ በመጠየቁ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ አልተከበረም።የአቶ ደጀኔ ጠበቃ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሻሩን ይቃወማሉ።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቱ በቀለ