የፌደሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምርጫን አስመልክቶ ውሳኔ አሳለፈ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 30 2012ማስታወቂያ
የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምርጫን በሚመለከት እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ክልሉ ያወጣው የምርጫ አዋጅ ከሕገ መንግሥት እንደሚቃረን ፣ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ስልጣን የሚጥስ መሆኑን ወስኗል።
የክልሉ ምክር ቤት አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ያስተላለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስት ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌደሬሽን ምክር ቤት ወስኗል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ