1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔና ተቃዋሚዎች

ረቡዕ፣ ሰኔ 3 2012

ምክር ቤቱ በዛሬዉ ጉባኤዉ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት መቀነሱ ከተረጋገጠ፣ ምርጫዉ ከ9 ወራት እስከ 1 ዓመት ባለዉ ጊዜ እንዲደረግ ወስኗል።ምርጫ እስኪደረግ በስልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት ከነሙሉ መዋቅሮቹ የያዘዉን ስልጣን እንደያዘ ይቀጥላል

https://p.dw.com/p/3dafm
Karte Äthiopien englisch

የደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔንና የተቃዋሚዎች ቅሬታ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጪዉ ነሐሴ ሊደረግ ታቅዶ የነበረዉ ምርጫ መራዘሙን የሐገሪቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ አፀደቀዉ።ለነሐሴ ተይዞ የነበረዉ ምርጫ የተሰረዘዉ በኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት መሐል ምርጫ ማድረግ አይቻልም በሚል ነዉ።ምክር ቤቱ በዛሬዉ ጉባኤዉ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት መቀነሱ ከተረጋገጠ፣ ምርጫዉ ከ9 ወራት እስከ 1 ዓመት ባለዉ ጊዜ እንዲደረግ ወስኗል።ምርጫ እስኪደረግ በስልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት ከነሙሉ መዋቅሮቹ የያዘዉን ስልጣን እንደያዘ ይቀጥላል።የምክር ቤቱን ዉሳኔ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከጥርጣሬና ትችት ጋር ተቀብለዉታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ