የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዘገባ
ማክሰኞ፣ ጥር 19 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በየክልሉ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ለማቅረብ ለሚያደርገዉ ጥረት የክልል መንግሥታት ባለመተባበራቸዉ ጥረቱ መታጎሉን አስታወቀ።የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሐኑ ፀጋዬ ዛሬ ለሕዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የ6 ወራት ዘገባ ሲያቀርቡ እንዳሉት በስም ያልጠቀሷቸዉ የክልል መንግስታት ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም።ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ እንደዘረዘሩት በተጠርጣሪዎች ብዛት በኒ ሻንጉል ጉሙዝ፣ደቡብ ኢትዮጵያና ኦሮሚያ መስተዳድሮች ከአንድ እስከ ሶስት ያለዉን ደረጃ ይይዛሉ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ