1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳይ መንግሥትና ግብረ ሠናይ ድርጅቶች

ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2011

ፈረንሳይ የሊቢያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ አዉሮጳ የሚሻገሩ ስደተኞችን እየተከታተሉ ለመያዝ የሚገለገሉባቸዉ 6 ፈጣን ጀልባዎችና ወታደራዊ ትጥቆችን ለመሸጥ ከሊቢያ ጋር ተዋዉላለች።

https://p.dw.com/p/3HWlr
Libyen Hunderte Flüchtlinge in Internierungslager ohne Versorgung
ምስል Reuters/H. Amara

የፈረንሳይ መንግስት፣ ስደተኞችና የመብት ተሟጋቾች

 

የፈረንሳይ መንግስት ሥደተኞችን እያደኑ የሚይዙ የሊቢያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎችን ለማስታጠቅ መወሰኑን የተለያዩ የመብት ተሟጋቾችና የርዳታ ድርጅቶች ተቃወሙት።ፈረንሳይ የሊቢያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ አዉሮጳ የሚሻገሩ ስደተኞችን እየተከታተሉ ለመያዝ የሚገለገሉባቸዉ 6 ፈጣን ጀልባዎችና ወታደራዊ ትጥቆችን ለመሸጥ ከሊቢያ ጋር ተዋዉላለች።አምንስቲ ኢንተርናሽናልና ድንበር የለሽ ሐኪሞችን ጨምሮ ስምንት የመብት ተሟጋቾችና የርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት የፈረንሳይ መንግስት ዉሳኔዉን ካልሻረ በሕግ ይፋረዱታል።

 ኃይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ