1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት በርሊን ገቡ

ሰኞ፣ ግንቦት 1 2014

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ለሁለተኛ ጊዜ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ የመጀመያ የውጭ ጉብኝታቸው ወደ በርሊን አድርገዉ፤ ከጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላቭ ሾልዝ ጋር በሩሲያ ዩክሬንን ወረራ ላይ እየተወያዩ ነው። ሁለቱ ሃገራት "ከዩክሬን ጋር እንደ አውሮጳውያን ቤተሰብ ጎን ለጎን እንቆማለን ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4B3Uz
Deutschland Frankreichs Präsident Macron trifft Bundeskanzler Scholz in Berlin
ምስል Lisi Niesner/REUTERS

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ለሁለተኛ ጊዜ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ የመጀመያ የውጭ ጉብኝታቸው ወደ በርሊን አድርገዉ፤ ከጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላቭ ሾልዝ ጋር  በሩሲያ ዩክሬንን ወረራ ላይ  እየተወያዩ ነው። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት በርሊን ላይ ከጀርመኑ መራሄ መንግሥት ከኦላቭ ሾልዝ ጋር ለስብሰባ የተቀመጡት፤ ሞስኮ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀበትን እና፤ ናዚ ጀርመን የተሸነፈበትን እለት በማስታወስ በተከበረበት እለት ነዉ። በርሊን ላይ በወታደራዊ ማርሽ አቀባበል የተደረገላቸዉ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ፤ ከቻንስለር ኦላቭ ሾልዝ ጋር በዝግ ስብሰባ እንደሚቀመጡ እና የእራት ሥነ-ስርዓትም እንዳላቸዉ የወጣዉ መረሐ ግብር ያሳያል።   

ሁለቱ መሪዎች ለዝግ ስብሰባ ከመቀመጣቸዉ በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የጀርመኑ ቻንስለር ሾልዝ የፈረንሳይ -ጀርመንን ወዳጅነት ከፍ አድርገዉ  ለጋዜጠኞች በአድናቆት መናገራቸዉ ተዘግቦአል። ጀርመን እና ፈረንሳይ "ከዩክሬን ጋር እንደ አውሮጳውያን ቤተሰብ ጎን ለጎን እንቆማለን ብለዋል። " ሾልዝ በመቀጠል "በታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ አጋጥሞናል ;እናም ከትብብራችን ልናገኘው የምንችለውን ትልቅ ጥንካሬ እያየን ነው" ብለዋል። በእነዚህ ቀናት እና ጊዜያት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ሃገሮች ድርጅት «ኔቶ» አባል ሃገራት ምን አይነት ብልፅግና፤ ምን አይነት ነፃነት እንዳለን እናቃለን፤ ይህ እሴታችንን ልንጠብቅ እና ልንከላከል ይገባል ብለዋል።  "አባል ሀገሮቻችን በዚህ ዘመን የሚያጋጥሙ ዋና ዋና ፈተናዎች በተሳካ ሁኔታ መፍታት የሚችሉት በጋራ ከቆሙ ብቻ ነው" ሲሉም አክለዋል።

ዛሬ ከቀትር በፊት በስትራስቡርግ ለአውሮጳ ፓርላማ ንግግር ያደረጉት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ  ህብረቱ በርካታ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ መጠየቃቸዉ ታዉቋል።  

 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ