1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የፀጥታው ምክር ቤት ዳግም በኢትዮጵያ ጉዳይ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 30 2014

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የአፍሪቃ ኅብረት የሚያደርገውን የሠላም ጥረት እንደሚደግፍ የፀጥታው ምክር ቤት ዐስታወቀ። የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ትናንት በኢትዮጵያ ጉዳይ ባደረገው ስብሰባ የአፍሪቃ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ባደረጉት ንግግር፦ ለሰላማዊ መፍትኄ ያለው ጊዜ እየጠበበ መምጣቱን አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/42mIC
USA | UN-Sicherheitsrat zu Äthiopien
ምስል Loey Felipe/UN Photo/Xinhua/picture alliance

«ሕገወጥ ብቻ ሳይሆን ከሥነ ምግባር ያፈነገጠ»

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የአፍሪቃ ኅብረት የሚያደርገውን የሠላም ጥረት እንደሚደግፍ የፀጥታው ምክር ቤት ዐስታወቀ። የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ትናንት በኢትዮጵያ ጉዳይ ባደረገው ስብሰባ  የአፍሪቃ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ባደረጉት ንግግር፦ ለሰላማዊ መፍትኄ ያለው ጊዜ እየጠበበ መምጣቱን አሳስበዋል። በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ታዬ  አጽቀስላሴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለፖለቲካዊ ውይይት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደምታከብር አመልክተዋል። ለአንድ ወገን ያደላ ያሉትን የምዕራቡ ዓለም ፖለቲከኞች፤ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የመገናኛ አውታሮች ተግባርንም፦ «ሕገወጥ ብቻ ሳይሆን ከሥነ ምግባር ያፈነገጠ» ሲሉ ኮንነውታል።  «ለምክር ቤቱ አባላት ላረጋግጥላችሁ የምሻው ሀገሬ ጥንትም በዚያ ሁሉ ባላንጣ ፊት እንዳሸነፈችው ሁሉ  ታሸንፋለች» ሲሉም ንግግራቸውን ቋጭተዋል። 

ታሪኩ ኃይሉ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

አዜብ ታደሰ