የጥምቀት በዓል አከባበር በአዲስ አበባ
ቅዳሜ፣ ጥር 11 2011ማስታወቂያ
የጥምቀት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሲከበር ውሏል። ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በጃንሜዳ በዓሉ ሲከበር ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የክልል አስተዳደሮች "እኛን ሊለያዩን እና ሰው መሆናችንን ሊያሳጡን አልተፈጠሩም" ሲሉ ተናግረዋል። ሰው በሰውነቱ ሊከበር እንደሚገባ ለጥምቀት በዓል ታዳሚያን አስረድተዋል። በዓሉ በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ እንደሆነ ታዳምያኑ ይናገራሉ።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ