1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥምቀት በዓል አከባበር በባቱ ደንበል ሐይቅ

ሐሙስ፣ ጥር 11 2015

ታይቶ በማይዘለቀው በደንበል ሃይቅ በቀድሞ ስሙ ዝዋይ ሃይቅ በጀልባ ታቦታትቱን ለማጀብ የሚደረገው ጉዞ በተለይም አመሻሹን አንስቶ በሚያፈርጠው ማዕበል የፍርሃት ስሜትን ብፈጥርም ድባቡ ግን ውብና አዝናኝም ጭምር ነው፡፡

https://p.dw.com/p/4MRUs
Äthiopien Timket Fest Ritual See Denbel
ምስል Seyoum Getu/DW

የጥምቀት በዓል አከባበር በደንበል ሐይቅ

                                  
ጥምቀት ባቱ ከተማ  ደንበል ሃይቅ ላይ የሚከበረው በልዩ ድባብ ነው፡፡ከሃይቁ አምስት ደሴቶች የሚወጡ ታቦታት ወደ ሃይቁ ዳርጃ ለማደር ሲጓዙ እና ዛሬ ወደየመንበራቸው ሲመለሱ በሃይቁ ላይ የሚቀዝፉ ጀልባዎች የሚያሳዩት ልዩ ትርዒት ትኩረትን የሚስቡ  ናቸው፡፡፡በዚህ በባቱ ከተማ ደንበል ሃይቅ ላይ ተከብሮ የዋለው በዓለ ጥምቀት ልዩ ቀለምና ገጽታ ያለው ነው፡፡ ታይቶ በማይዘለቀው በደንበል ሃይቅ በቀድሞ ስሙ ዝዋይ ሃይቅ በጀልባ ታቦታትቱን ለማጀብ የሚደረገው ጉዞ በተለይም አመሻሹን አንስቶ በሚያፈርጠው ማዕበል የፍርሃት ስሜትን ብፈጥርም ድባቡ ግን ውብና አዝናኝም ጭምር ነው፡፡ 
በደንበል ሃይቅ አምስት ደሴቶች ላይ የሚገኙ አድባራትን ጨምሮ በባቱ ከተማ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ደብራት የከተራ ለት ታቦታቱን የሚያሳርፉት በዚሁ ሃቅ ዙሪያ ነው፡፡ ስድስት ደብራት ታቦታት ያረፉበት የባቱ ከተማ የደንበል ሃይቅ ዳርቻ የባህረ ጥምቀት ማክበሪያ ስፍራ ጥምቀትን በባቱ ማራኪ ካደረጉ ስፍራዎች አንደኛው ነው፡፡
የሃይማኖት መምህር ቢኒያም ታደለ የባቱ ሃመረ-ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አገልጋይና የካህናት ማሰልጠኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተጠሪ ናቸው፡፡ “ስድስት ደብራት በሚያርፉበት በዚህ ስፍራ ብቻ እጅግ በርካታ ምዕመናን በዓለ ጥምቀቱን ያደምቃሉ” ያሉን እኚህ መምህር የበዓለ ጥምቀት መንፈሳዊ ትርጓሜው ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ በማቅናት የተጠመቀው ጥምቀት መታሰቢያ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሌላው አስተያየት ሰጪያችን ከአዲስ አበባ ጥምቀትን ለማክበር ባቱ የተገኙት ዲያቆን መርዕድ ቱሉ ናቸው፡፡ “የሰው ልጆች የሃጥያት ደብዳቤ የተቀደደበት ክርስቶስም በውሃ ውስጥ ቆሞ ለሰው ልጅ ድህነት ሃጥያትን ያስተሰረየበት ነው” በማለት የጥምቀትን መንፈሳዊ አንድምታ በማብራራትም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በዓሉ የሚሰጠውን ትልቅ አንድምታ አንስተዋል፡፡
ከሃይማኖታዊ ትሁፊቱ ባሻገር ጥምቀት ድንቅ የቱሪስት መስዕብ ወደ መሆን መሸጋገሩ፤ የበዓሉን እሴቶች በሚገባ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው ይላሉም አስተያየት ሰጪዎቹ፡፡ 
ጥምቀት በባቱ የተለየ ገጽታ ያለውና የጥምቀትን የውሃ በዓልነት የሚያረጋግጥ ነው የሚሉት ዲያቆን መርዕድ ቱሉ በበኩላቸው፤ ከተሰራበት የደንበል ሃይቅ ለጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ድምቀት በተጨማሪ እንደ አጓጊ መስዕብ መጠቀምም የሚቻል ነው ብለዋል፡፡ 
ከትናንት ጀምሮ በከተራ በዓል እንዲሁም ዛሬ በበዓለ ጥምቀት ተከብሮ የዋለው የባቱ ደንበል ሃይቅ ባለ ልዩ ትዕይንት የጥምቀት በዓል አከባበር በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኦሮሚያን ይጎብኙ መርሃግብር ቦታውን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራም ነው ተብሏል፡፡ 

ለጥምቀት በዓል ጀልባዎች በደንበል ሐይቅ ላይ ሲቀዝፉ
ለጥምቀት በዓል ጀልባዎች በደንበል ሐይቅ ላይ ሲቀዝፉምስል Seyoum Getu/DW
የጥምቀት በዓል አክባሪዎች በደንበል ሐይቅ
የጥምቀት በዓል አክባሪዎች በደንበል ሐይቅምስል Seyoum Getu/DW

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ