1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ቁጥጥር አዋጅ ፀደቀ

ሐሙስ፣ የካቲት 5 2012

የኢትጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ 5 ስብሰባ ሲያነጋግር የቆየውን የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን የተመለከተውን ረቂቂ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ።

https://p.dw.com/p/3Xjko
Äthiopien Addis Ababa | Parlament diskutiert Anti-Hassrede und Missinformationsgesetz
ምስል DW/Y. Gebrezihaber

ረቂቂ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል

የኢትጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ 5 ስብሰባ ሲያነጋግር የቆየውን የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን የተመለከተውን ረቂቂ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ። በንግግር ነጻነት ላይ ተጽእኖን ሊያሳድር ይችላል ተብሎ በተለያዩ ወገኖች ትችት ሲቀርብበት የነበረው ይህ ረቂቅ ሕግ፤ ከምክር ቤቱ አባላት 23 የተቃውሞ ድምጽ ገጥሞታል። 2 ድምጸ ተዐቅቦም ተመዝግቧል። በምክር ቤቱ እንደተጠቀሰው በረቂቅ ሕጉ ላይ አንዳንድ ክለሳዎች መደረጋቸውም ተገልጿል። ቢሆንም ግን አሁንም አንዳንድ ግልጽነት የሚጎላቸው ሐሳቦች እንዳሉትም ተነስቶ ነበር ተብሎአል። የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁን በአብላጫ ድምጽ አጽድቆአል። ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ልዝርዝር ምርመራ ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ መርቶታል።  ይህ ሕግ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የፈጠረው ስጋትን ምን ይሆን? የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት አዋጅ መጽደቅን ተከትሎ በኢትዮጵያ የመብቶችና ዴሞክራሲ ብልጽግና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በፈቃዱ ኃይሉን ጠይቀነዋል። የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሰ  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ