1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ምስረታ እና ሙያዊ ፋይዳው

ቅዳሜ፣ መስከረም 14 2015

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ይሁኝታ መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ተመስርቷል፡፡ የሙያ ማህበሩ ምስረታ ዋነኛ ዓለማው በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት እንከኖችን ለማረምና የሙያተኛውን ጥቅም ማስከበር ላይ ማተኮር መሆኑንም የማህበሩ መስራች ኃላፊዎች እና አባላቱ ይገልጻሉ፡፡

https://p.dw.com/p/4HIRX
The establishiment of health professionals  association
ምስል Seyoum Getu/DW

የጤና ባለሞያዎች ማህበር ተመሰረተ

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ምስረታ እና ሙያዊ ፋይዳው

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ይሁኝታ መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ተመስርቷል፡፡

የሙያ ማህበሩ ምስረታ ዋነኛ ዓለማውን ያደረገም ሙያውን ማሳደግ፤ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት እንከኖችን ለማረምና የሙያተኛውን ጥቅም ማስከበር ላይ ማተኮር መሆኑንም የማህበሩ መስራች ኃላፊዎች እና አባላቱ ይገልጻሉ፡፡

የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ የሙያ ማህበሩ ምስረታ ለዘርፉ ይዞ ስለሚመጣው ጥቅም አጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም. እውቅና አግኝቶ ትናንት መስከረም 13 ቀን 2013 ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ህጋዊ ሰውነቱን ተቀብሏል፡፡

The establishiment of health professionals  association
ምስል Seyoum Getu/DW

የማህበሩ መስራች ጉባኤ ሰብሳቢ የሆኑት ነርስ ጳውሎስ ብርሃነ ከ79 ሺህ በላይ በሙያው የተሰማሩ አባላት እንዳሰባሰበ የገለጹት፤ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በሙያው ስር የሚገኙና በተለያዩ የሙያው ዘርፎች የተደራጁ ማህበራትንም ጭምር አንድ ላይ ለማገናኘት ያለመ ነው፡፡ 

አንደ የህክምና ባለሙያውና የማህበሩ መስራች ጉባኤ ሰብሳቢው ማብራሪያ ከዚህ በፊት በተለያዩ የሙያው ዘርፎች ተደራጅተው ማህበር መስርተው የነበሩ የባለሙያዎች ማህበራት ሊፈቱዋቸው ያልቻሉ የህክምና ዘርፍ ማነቆዎች እና የባለሙያዎች ጥያቄን ለመፍታት የተመሰረተው የአዲሱ ማህበር ስራ ይሆናል፡፡ በየትኛውም ዘርፍ ውስጥ ያለው የሙያው አባላትን አንድ ላይ በማምጣት የተሻለ አቅም መፍጠር ደግሞ እንደ መነሻ ተወስዷል፡፡

ዶ/ር ሜሮን ሰለሞን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጠቅላላ ሃኪም እና የአዲሱ የጤና ባለሙያዎች ማህበር አባል ናቸው፡፡ ማህበሩ በሙያው ስር የሚገኙ የተለያዩ ዘርፎችን ማሰባሰቡ በዚሁ ዙሪያ ለሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ለማስገኘት አቅም እንደሚፈጥርም ነው እምነታቸውን የሚገልጹት፡፡

The establishiment of health professionals  association
ምስል Seyoum Getu/DW

የሙያውን፣ የባለሙያ እና የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ወጥኖ እንደተመሰረተ የሚነገረው የጤና ባለሙያዎቹ ማህበር ዓለማውን ከግብ ለማድረስም እስካሁን ከ300 በላይ ጊዜያዊ አስተባባሪዎችን ወደ ስራ ማሰማራቱን ይገልጻል፡፡ እንደ የማህበሩ መስራች ጉባኤ አስተባባሪ ነርስ ጳውሎስ ብርሃነ፣ ማህበሩ የአጭር እና ረጂም ጊዜ እቅዶችም ይኖሩታል፡፡

እንደ ባለሙያዎቹ አስተያየት አሁን ህጋዊ እውቅና አግኝቶ የተመሰረተው ሙያዊ ማህበሩ በቀጣይ በየደረጃው ሙያተኛው ለሚያነሷቸው ጥያቄ እና ዘርፉ ላይ ለሚስተዋሉ የሙያ ግድፈቶች እልባትን ለማፈላለግ አተኩሮ ይሰራል፡፡ እንደ ባለሙያዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎች የሙያውን ስነምግባር ባልጣሰና ስራን ሳይጎዱ ኃላፊነትን ሳያጎድፉ በሆነ አኳን እንዲሆን ማህበሩ የተጣለበት ኃላፊነት ነውም፡፡

በኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ከደመወዝ ጭማሪ እና ከሙያተኞች ጥቅማጥቅም ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡  

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ