1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት መግለጫ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 20 2013

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ሁለቱ አገራት የጋራ በሚያደርጓቸው የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ገዳዮች ዙሪያ ለመምከር መምጣታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3zWDu
Äthiopien Logo Prime Minister Office

ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ሁለቱ አገራት የጋራ በሚያደርጓቸው የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ገዳዮች ዙሪያ ለመምከር መምጣታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ሳልቫኪር ሕወሓት በሰሜን ዕዝ የጦር ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘው የፌዴራል መንግስት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ያደረገውን ጥረት ማድነቃቸው በመግለጫው ተጠቅሷል። ኃላፊዋ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተም የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ አፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች መድረስ መቀጠሉን ገልፀዋል።ሕወሓት በአፋርና አማራ ክልሎች ላይ ንፁሃንን መግደሉን፣ ማፈናቀሉን፣ የመንግስትና የግለሰቦችን ንብረት ማውደሙን መቀጠሉንም ቢልለኔ ሥዩም ተናግረዋል። መግለጫው የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት በመገኘት የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ