1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚንስትሩ የሰላም ጥሪ ፤ ሰላማዊ ምላሽ እንዴት ያግኝ?

እሑድ፣ ግንቦት 11 2016

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንታት መንግስታቸው ከታጣቂዎች ጋር ብርቱ ፍልሚያ እያደረገ ወደ ሚገኝባቸው የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አካባቢዎች አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሁለቱም አካባቢዎች በጥቅሉ ጦርነት እንዲቆም ብሎም «በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ መገዳደልም እንዲያበቃ » ጥሪ አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/4g36p
Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Englisch

የጠቅላይ ሚንስትሩ «የሰላም ጥሪ » ምን አይነት ምላሽ ያግኝ ?

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንታት መንግስታቸው ከታጣቂዎች ጋር ብርቱ ፍልሚያ እያደረገ ወደ ሚገኝባቸው የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አካባቢዎች አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ሁለቱም አካባቢዎች ሲጓዙ ለተለያየ ዓላማ ቢሆንም ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል። በጥቅሉ ጦርነት እንዲቆም ብሎም  «በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ መገዳደልም እንዲያበቃ » ጥሪ አስተላልፈዋል። 

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ሁለቱም አካባቢዎች ሲጓዙ ለተለያየ ዓላማ ቢሆንም ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል።ምስል United Nations FAO 2024

 

በጥቂት ቀናት ልዩነት ወደ አማራ ክልል መዲና ያቀኑት ጠቅላይ ሚንስትሩ የአባይን ድልድይ መርቀው ሲከፍቱ «ጫካ» ለሚገኙ ኃይሎች “በማይገባ ነገር መገዳደል ይብቃን” የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለታጣቂዎች ያቀረበዉ ጥሪና ተግዳሮቱ

በቅድሚያ ለአስተዳደራቸው በተጠራ «የድጋፍ ሰልፍ» ላይ ለመታደም ነቀምቴ ስቴዲየም ለተሰበሰበ ህዝብ ባደረጉት ንግግር «የኦሮሞ ሕዝብ መብቱን ለማስከበር ለበርካታ ዓመታት ባደረገዉ ትግል ብዙ ሺዎች  መስዋዕትነት ከፍለዋል። ያዘመን ግን ዛሬ አልፏል። ኦሮሞ ነፃ ወጥቷል።» ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም የኦሮሞ ህዝብ አንድ እንዲሆን እና በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ መገዳደል እንዲቆም አውጀዋል።

ባህር ዳር ከተማ ውስጥ የተገነባው አዲሱ የአባይ ድልድይ
ወደ አማራ ክልል መዲና ያቀኑት ጠቅላይ ሚንስትሩ የአባይን ድልድይ መርቀው ሲከፍቱ «ጫካ» ለሚገኙ ኃይሎች “በማይገባ ነገር መገዳደል ይብቃን” የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

 

በሌላ በኩል በጥቂት ቀናት ልዩነት ወደ አማራ ክልል መዲና ያቀኑት ጠቅላይ ሚንስትሩ የአባይን ድልድይ መርቀው ሲከፍቱ «ጫካ» ለሚገኙ ኃይሎች “በማይገባ ነገር መገዳደል ይብቃን” የሚል ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከመንግስታቸው ጋር በመፋለም ላይ ያለውን የፋኖ ታጣቂ ቡድን በስም ባይጠቅሱም «ድልድይ የሌለው ጉዞ ይብቃን  ኑ ወደ ክልላችሁ ተመለሱ፣ ከፕሬዚዳንታቹ ጋር ሆናችሁም ክልላችሁን አልሙ» ብለዋል።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት የሰላም ጥሪ፣ ተስፋና ስጋቱ

በኦሮሚያ ክልል መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር እያደረገ  ባለው ጦርነት ብርቱ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት አስከትሎ አሁንም ድረስ መፍትሄ ሳይገኝለት ቀጥሏል። በክልሉ ጦርነቱ አይሎ በሚደረግባቸው አካባቢዎች በማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ህዝቡ «ነጻ ላውጣህ » ከሚለውም ሆነ «ላስተዳድርህ» ከሚለውም ወገን ተስፋ እስከመቁረጥ እና አዳኙን ከሌላ እስከመጠበቅ አድርሶታል። በአማራ ክልልም የፋኖ ታጣቂዎች በይፋ ከመንግስት ጋር ጦርነት ከገጠሙ እነሆ አንድ ዓመት እየሞላው ነው። በጦርነቱ በተመሳሳይ በክልሉ ብርቱ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል።

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት የሰላም ጥሪ

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግስት ከታጣቂዎች ጋር የሰላም ንግግር በሚያደርግበትም ሆነ የሰላም ጥሪ በሚያስተጋባበት ወቅት በየአካባቢው ጦርነት ለአፍታ በማይገታበት ሁኔታ የሰላም ንግግሩም ሆነ ጥሪው  ከለይስሙላ አያልፍም የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም ። በዚያው ልክ ታጣቂዎቹም ችግራቸውን በንግግር ለመፍታት ያላቸው ፍላጎት የሀገሪቱን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተስፋ አያሳድርም።

ታምራት ዲንሳ