የአቶ ኃይለ ማርያም መነሳት እና ፋይዳው
ሐሙስ፣ የካቲት 8 2010ማስታወቂያ
ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በስልጣን በቆዩባቸው አመታት ኢትዮጵያ በተቃውሞ ስትታመስ ቆይታለች። በርካቶች ሞተዋል፤ ታስረዋልም። ገዢው ግንባር ኢሕአዴግ በአገሪቱ የታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የማሻሻያ እርምጃዎች እንደሚወስድ ቃል ሲገባ ቆይቷል። አባል ድርጅቶቹ እርስ በርስ መተማመናቸው ጎድሎ እንደነበር ሊቃነ-መናብርቱ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የአገሪቱን መረጋጋት ለመመለስ የጠቅላይ ምኒስትሩ ከስልጣን መልቀቅ ምን ፋይዳ ይኖረዋል? የፖለቲካ ተንታኝ ቻላቸው ታደሰን እሸቴ በቀለ በስልክ አነጋግሯቸዋል። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡ።