የጠ/ሚኒስትሩ መልዕክት እና የተቃዋሚዎች አስተያየት
ሰኞ፣ ግንቦት 20 2010ማስታወቂያ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የግንቦት 20 መልዕክት በስድስት ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር። ሁሉም ሰው ወደራሱ ተሰዶ ራሱን በጽሞና እንዲመለከት እና ያሸናፊነት ስነ ልቦና እንዲላበስ ከጎረቤቶቻችን ከቅርብ ወዳጆቻችን ጋር ያሉ ክፍተቶችን በእርቅ መሙላት፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ የታረዙትን በማልበስ እና ደካሞችን በማገዝ መከበር እንዳለበት ጠቁመዋል። የንባብ ባህላችንን በማዳበር፣ የግል እና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅ እንዲሁም ለሴቶች ክብር በመስጠት ግንቦት 20ን ልናከብረው ይገባልም ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት እንዴት አገኛችሁት ብለን ከጠየቅናቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል የመኢአድ ሊቀመንበር ዶ/ር በዛብህ ደምሴ፣ የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ እንደዚሁም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ምላሻቸውን ሰጥተውናል። ሶስቱም የፓርቲ መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ከዚህ ቀደም ከነበረው የተለየ መሆኑን ጠቅሰው ድጋፍ የሚቸረው አይነት እንደሆነ ተናግረዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ