የጠ/ሚንስትሩ የፍራንክፈርት ስብሰባ እና አንደምታው
ረቡዕ፣ ጥቅምት 21 2011ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በጀርመን ፍራንክፈር ከተማ ላይ ለተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ንግግር አደርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀርመን ዛሬ ለደረሰችበት የኤኮኖሚ ደረጃ የበቃችው ዜጎቿ ወገባቸውን አሥረው ተስፋ መቁረጥን አባርረው፤ የደረሰባቸውን መከራ ሁሉ ለነገ ሲሉ ታግሰው ለሀገራቸው አንድ ሆነው በትጋት ስለሠሩ መሆኑን አመልክተዋል። ዛሬ በአውሮጳ በሚገኙ ወገኖች ፊት ሲቆሙ በኢትዮጵያ ችግሩም ሆነ ግጭት ጠፍቶ ቢሆን እጅግ ይደሰቱ እንደነበር ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሁንም ግን ሁለት ነገሮች አሉን ሲሉ ንግግራቸውን ቀጥለዋል። ከዚህም ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀርመን እና ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት በፍራንክፈርት ኮሜርስ አረና ስታዲየም ለተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ጠንክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።
ነጋሽ መሀመድ
አዜብ ታደሰ