1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚኒስትሩ ውይይት በወላይታ

ሰኞ፣ ሐምሌ 22 2011

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በወልይታ ሶዶ ተገኝተው ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ማካሄዳቸው ተሰምቷል። በውይይቱ ወቅት ከተነሱት ነጥቦች መካከልም የወላይታ የክልል አደረጃጀት ያስፈልጋል የሚለው ዋነኛው መሆኑን የወላይታ ዞን መስተዳድር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ «DW» ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3Mv3V
Karte Sodo Ethiopia ENG

«በውይይቱ ወቅት ከተነሱት ዋነኛው የክልልነት ጥያቄ ነው።»

 በተለይ ከአንድ ሺህ ከሚበልጡ የወላይታ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባካሄዱት ውይይት በክልል ለመደራጀት ጥያቄ የሚያነሱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጉዳትና ጥቅሙን በሰከን መንገድ ሊመረምሩ እንደሚገባ ማመልከታቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ክልል ባደረጉት ጉብኝት የአረንጓዴ አሻራ ቀን በሚል ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ 200 ሚሊየን ችግኝ የመትከልን ዘመቻ በማስጀመር ነው ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደረጉት። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

 እሸቴ በቀለ