1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ዐቢይ የአፍሪቃ ሃገራት ጉብኝት እና አንድምታዉ

ሰኞ፣ ነሐሴ 24 2013

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባለፉት ሁለት ቀናት በጎረቤት አገራት ርዋንዳ እና ኡጋንዳ የሥራ ጉብኝት አድርገው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

https://p.dw.com/p/3zgfT
Äthiopien Ministerpräsident Abiy Ahmed trifft Ruandas und Ugandas Staatsoberhäupter
ምስል Lubega Emmanuel/DW

ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ ትኩረት ትሰጣለች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባለፉት ሁለት ቀናት በጎረቤት አገራት ርዋንዳ እና ኡጋንዳ የሥራ ጉብኝት አድርገው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን በማኅበራዊ መገናኛ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ ትኩረት ትሰጣለች የሚለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉብኝትም ይህንን የማጠናከር ዓላማ ያለው ነው ብሏል።

አንድ የዲፕሎማሲ ተመራማሪ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ያደረጉት ይህ ጉብኝት አንድም መንግሥት አገሪቱ ውስጥ ያለውን ግጭት በተወሰነ ደረጃ መቋቋም መቻሉን የሚያሳይ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ለምትፍልጋቸው ጉዳዮች ወዳጆች ናቸው ብላ ከምታስባቸው አገሮች ጋር ግንኙነቷን የበለጠ ለማጠናከር የሚደረግ እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል ብለዋል።

 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ