1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የጣልያን ይፋዊ ጉብኝት

ሰኞ፣ ጥር 13 2011

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጣሊያን ሮም የሚገኙት የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቃነ-ጳጳሳት ፋራንሲስ ጋር ቫቲካን ላይ መገናኘታቸዉን የቫቲካን ቢሮ አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ቫቲካንን ሲጎበኙ ይህ የመጀመርያቸዉ ነዉም ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/3BvPz
Vatikanstaat Papst Franziskus & Abiy Ahmed, Premierminister Äthiopien
ምስል Vatican News

የአዉሮጳ ኅብረትን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጣሊያን ሮም የሚገኙት የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቃነ-ጳጳሳት ፋራንሲስ ጋር ቫቲካን ላይ እንደተገናኙ የቫቲካን ቢሮ አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ቫቲካንን ሲጎበኙ ይህ የመጀመርያቸዉ ነዉም ተብሎአል። በሌላ በኩል እዝያዉ ሮም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሊ እና ከተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆዜ ግራዚያኖ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዝዳንት ጊልበርት ሆውንግቦ ጋር ተገናኝተዉ ተወያይተዋል። የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ዛሬ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ነገ ስዊዘርላንድ ላይ በሚጀመረዉና እስከ ፊታችን አርብ በሚዘልቀዉ 49 ኛዉ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚክ ፎረም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይሳተፋሉ ተብሎም ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በዚሁ ሳምንት የአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ ብረስልስም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በዚሁ ሳምንት የአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ ብረስልስ ላይ የአዉሮጳ ኅብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፌደሪካ ሞጎሮኒ እና ከኅብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተዉ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Italien Abiy Ahmed, Premierminister Äthiiopien & Giuseppe Conte in Rom
ምስል Office of the Prime Minister of Ethiopia

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ