1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ዐቢይ በፍቅር የመደመር ጉዞ አውሮጳ

ሰኞ፣ ጥቅምት 12 2011

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ " አንድ ሆነን እንነሳ ነገንም እንገንባ " በሚል መሪ ቃል በመላው አውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያያ ጋር ጥቅምት 21፤ 2011 ዓ.ም በጀርመን የፍራንክፈርት ከተማ ለሚያካሂዱት ውይይት ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት እና የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ገለጹ።

https://p.dw.com/p/36xYa
Dr. Abiy Ahmed
ምስል DW/S. Teshome

«አንድ ሆነን እንነሳ፤ ነገንም እንገንባ» የለውጡ ኃይል መሪ ቃል

 በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትሩን  መምጣት በጉጉት  ብንጠብቅም  ላለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ሲፈጸም የነበረውን  የመብት ረገጣ  የዲሞክራሲ  እጦት  እና  አፈና  በመቃወም  አሁን  ለመጣው  ለውጥ የበኩላችንን  እገዛ  ስናበረክት የቆየን  በአቀባበሉ  ጊዜያዊ  አስተባባሪ  ኮሚቴ  ውስጥ  የበኩላችንን ተሳትፎ  እንዳናደርግ  ዕድል ተነፍጎናል ፤  ዲያስፖራውን  ሲከፋፍሉ  የነበሩ  ግለሰቦች  በኮሚቴው ውስጥ  መካተታቸውም  በአገሪቱ  የተጀመረውን  በፍቅር  የመደመር  ጉዞ  መርህ  እንዳያሰናክሉት ስጋት  አለን  ሲሉ  ቅሬታቸውን  የሚያሰሙ አሉ።  የኢትዮጵያ  ኤምባሲ  ቆንጽላ  ጽህፈት ቤት  ጄኔራል አቶ ምህረተዓብ  ሙሉጌታ እና  የዝግጅቱ ጊዜያዊ  ኮሚቴ  የሚድያ እና  ሕዝብ ግንኙነት  አስተባባሪ አቶ ዘለዓለም  ደበበ  በበኩላቸው  ቅሬታው  አስተባብለዋል::  ዝርዝሩን  እንዳልካቸው  ፈቃደ አጠናቅሮታል::

እንዳልካቸው  ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ