1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎሮ-አዲስ አበባ ነዋሪ ስሞታ

ረቡዕ፣ መስከረም 16 2011

ሰሞኑን ከጥቃት ያመለጡ አንድ የአካባቢዉ ነዋሪ እንዳሉት በቡድን የተሰበሰቡ ወጣቶች በተለይ ማታ በየመንገዱ ዳርቻ እያደፈጡ ወደየቤቱ የሚገባዉን ነዋሪ ያጠቃሉ፤ ይዘርፋሉም።

https://p.dw.com/p/35XBV
Äthiopien Stadt Mekelle
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

(Beri.Brussels) Attack and Insecurity in Goro-AA - MP3-Stereo

አዲስ አበባ ዉስጥ በልማዱ ጎሮ ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ ነዋሪዎች የሚፈፀምባቸዉ ዘረፋ እና ድብደባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱን አስታወቁ።ሰሞኑን ከጥቃት ያመለጡ አንድ የአካባቢዉ ነዋሪ እንዳሉት በቡድን የተሰበሰቡ ወጣቶች በተለይ ማታ በየመንገዱ ዳርቻ እያደፈጡ ወደየቤቱ የሚገባዉን ነዋሪ ያጠቃሉ፤ ይዘርፋሉም።የአካባቢዉ ፖሊስም በነዋሪዎች ላይ የሚፈፀመዉ ድብደባ እና ዘረፋ መደጋገሙን አረጋግጧል።የአካባቢዉ ፖሊስ አዛዥ እንዳሉት የመንገድ ዳር መብራቶች አለሞኖር እና የሰዉ ኃይል እጥረት የፖሊስን የቁጥጥር ሥራ አስቸጋሪ አድርጎታል።

ዳግማዊ ሲሳይ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ