1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎርፍ አደጋና ስጋት በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ነሐሴ 14 2013

አንዳድ ቀን ፀኃዩ ገርሮ ነዋሪዉን ሲያማርር ይዉልና በማግስቱ ወይም በሌለኛዉ ቀን በረዶ የቀላቀለ ከባድ ነጎድጓዳማ ዝናብ ባካባቢዉን ይወርዳል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚትርዮሎጂ ኤጄንሲ እንደሚለዉ ደግሞ ከባዱ ዝናብ እስካሁን ካደረሰዉ ጉዳት በላይ ሊያደርስ ይችላል

https://p.dw.com/p/3zHex
Äthiopien, Addis Ababa | Starke Überschwemmungen
ምስል Mesay Tekelu/DW

የክረምቱ ዝናብ በማየሉ እስካሁን ከደረሰዉ በላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል-ሚትሪዮሎጂ

የዘንድሮዉ ክረምት ዝናብ ኢትዮጵያ ዉስጥም የሰዉ ሕይወት፣ ሐብትና ንብረት እያጠፋ ነዉ።ግራ አጋቢዉ የዝናቡ ማየል አይደለም።አንዳድ ቀን ፀኃዩ ገርሮ ነዋሪዉን ሲያማርር ይዉልና በማግስቱ ወይም በሌለኛዉ ቀን በረዶ የቀላቀለ ከባድ ነጎድጓዳማ ዝናብ ባካባቢዉን ይወርዳል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚትርዮሎጂ ኤጄንሲ እንደሚለዉ ደግሞ ከባዱ ዝናብ እስካሁን ካደረሰዉ ጉዳት በላይ ሊያደርስ ይችላል።የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ  ጫሊ ደበሌ  ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት በእስካሁኑ ዝናብ ወንዞችና ኮሬዎች እየሞሉ፣መሬቱን እየረጠበ በመሆኑ ተጨማሪ ዝናብ ሲጥል አደገኛ ጎርፍ ማስከተሉ አይቀርም።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ