የግል ትምህርት ቤቶች ወርኃዊ ክፍያ ቁጥጥር በድሬደዋ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 26 2013ማስታወቂያ
በድሬደዋ የሚገኙ 68 ያህል የግል ትምህርት ቤቶች በወርሀዊ ክፍያ ላይ ያደረጉት የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ ጥናት በማድረግ የክፍያ ተመን መውጣቱን የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በዚህ ውሳኔ መሰረት ማንኛውም የግል ትምህርት ቤት በወርሀ ክፍያ ላይ 30 በመቶ እንዲሁም ለመመዝገቢያ ክፍያ ከ25 በመቶ በላይ ማስከፈል እንደማይችሉ ገልጿል። የኅብረተሰቡ ገቢ ለውጥ ባላመጣበት በአስተዳደሩ የተጨመረው ጭማሪ ተመንም ቢሆን አግባብ ባይሆንም በአንፃሩ የተሻለ ውሳኔ በመሆኑ አተገባበሩ ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ ወላጆች ጠይቀዋል።
መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ