1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋምቤላ ፀጥታና የክልሉ የምርጫ ዝግጅት 

ሰኞ፣ ግንቦት 9 2013

አቶ ቶማስ ከደቡብ ሱዳን ደንበር ተሸጋሪ የህገወጥ መሳሪያ የሀሰተኛ የገንዘብ ዝውውር ለክልሉ ፈተና እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ከህገወጥ መሳሪያና ሐሰተኛ የገንዘብ ዝውውር ጋር የተያያዘውን ችግር ለመከላከል ከአጎራባች ክልሎች ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል፡፡

https://p.dw.com/p/3tWCo
Äthiopien | Stadt Gambella
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የጋምቤላ ፀጥታና የክልሉ የምርጫ ዝግጅት 

መጪው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጋምቤላ ክልል መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ የክልሉ መንግስት አስታወቀ፣ ከዚህ በፊት ይታዩ የነበሩ የጎሳ ግጭቶች ተወግደው ክልሉ አሁን ሰላም የሰፈነበት እንደሆነ የጋምቤላ ክልል የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፣ የደንበር ተሻጋሪ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር ግን ለክልሉ ፈተና እንደሆነም ቢሮው ገልጧል፡፡

የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት ሰሞኑን ባሕር ዳር ውስጥ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት መጪው አገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል፡፡ 
በክልሉ ከእቅድ በላይ መራጮች መመዝገባቸውንና በክልሉ 431 ምርጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ 6 የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫው ይወዳደራሉ።በክልሉ ከዚህ በፊት ይታዩ የነበሩ የጎሳ አመለካከቶች ተወግደው አሁን ከሌሎች ክልሎች በተሸለ ሁኔታ ክልሉ ሰላም ሰፈነበት እንደሆነም አቶ ቶማስ አመልክተዋል፡፡ 
መደበኛ ያልሆኑና ክልሉን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የሚወስዱ ጅምሮችን በጊዜ ማስተካከል መቻሉ ሌላው በክልሉ ሰላም ለማምጣት ከተሰሩ ሰራዎች አንዱ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ድንበር እየተሻገሩ ህፃናትን ይወስዱ የነበሩ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላትንም በቅንጅት መሰራት በመቻሉ በዚህ ዓመት አንድም ህፃን እንዳልተወሰደ ቢሮ ኃላፊው አብራርተዋል፡፡ ከደቡብ ሱዳን ደንበር ተሸጋሪ የህገወጥ መሳሪያ የሀሰተኛ የገንዘብ ዝውውር ለክልሉ ፈተና እንደሆነ አስረድተዋል፡፡እንደ አቶ ቶማስ ከህገወጥ መሳሪያና ሐሰተኛ የገንዘብ ዝውውር ጋር የተያያዘውን ችግር ለመከላከል ከአጎራባች ክልሎች ጋር በጋራ እየተሰራ ነው፡፡የጋምቤላ ክልል 5 ነባር ብሔረሰቦችን የያዘ ሲሆን ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት አብዛኘው ቆላማ የሆነ የአገሪቱ አካባቢ ነው፡፡ 
ዓለምነው መኮንን 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ