የጊብሰን አካደሚ ዳይሬክተር ለመምህራን ወቀሳ የሰጡት ምላሽ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 10 2010ማስታወቂያ
አስሩ ከተለያዩ የትምህርት ቤቱ ቅርንጫፎች የተባረሩት መምህራን ትምህርት ቤቱ የጥራት ጉድለት የሚታይበት የትምህርት ስርዓት እንደሚከተል እና የሰራተኞችንም መብት እንደማያከብር በግልጽ በመናገራቸው ከስራ ገበታቸው እንደተባረሩ ነው የተናገሩት። ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር ዛቻ፣ ማስፈራራት እና የደሞዝ ቅጣትም እንደደረሰባቸውም መምህራኑ አስታውቀዋል። ይሁንና፣ የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ አቶ ኡመር አሊ ለዶይቸ ቬለ እንደገለጼት፣ መምህራኑ ከስራ የተባረሩት የዲሲፕሊን ግድፈት በማሳየታቸው ነው፣ ትምህርት ቤቱም አንዳችም የትምህርት ስርዓት ጥሰት አልፈጸመም።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ